-
“የማይታየው” አምላክ ይታይሃል?መጠበቂያ ግንብ—2014 | ሚያዝያ 15
-
-
10. (ሀ) ይሖዋ በ1513 ዓ.ዓ. ኒሳን ወር ላይ ለእስራኤላውያን ምን መመሪያ ሰጣቸው? (ለ) ሙሴ የአምላክን መመሪያዎች የታዘዘው ለምንድን ነው?
10 በ1513 ዓ.ዓ. በኒሳን ወር ላይ ሙሴና አሮን ለእስራኤላውያን እንግዳ የሆነ መመሪያ እንዲሰጡ ይሖዋ አዘዛቸው፤ መመሪያው እስራኤላውያን እንከን የሌለበት በግ ወይም ፍየል በማረድ ደሙን በበራቸው መቃንና ጉበን ላይ እንዲቀቡ የሚያዝዝ ነበር። (ዘፀ. 12:3-7) ታዲያ ሙሴ ምን አደረገ? ሐዋርያው ጳውሎስ ከጊዜ በኋላ ስለ ሙሴ እንዲህ በማለት ጽፏል፦ “አጥፊው የበኩር ልጆቻቸውን እንዳይገድል ሙሴ ፋሲካን ያከበረውና መቃኖቹ ላይ ደም የረጨው በእምነት ነው።” (ዕብ. 11:28) ሙሴ፣ ይሖዋ እምነት የሚጣልበት አምላክ እንደሆነ ያውቅ ነበር፤ በመሆኑም ይሖዋ፣ የግብፃውያንን የበኩር ልጆች ለመግደል የገባውን ቃል እንደሚፈጽም እምነት ነበረው።
11. ሙሴ ሌሎችን ያስጠነቀቀው ለምንድን ነው?
11 የሙሴ ልጆች በወቅቱ በምድያም የነበሩ ይመስላል፤ ይህ ቦታ የሚገኘው ደግሞ ‘ከአጥፊው’ ርቆ ነው።a (ዘፀ. 18:1-6) ያም ሆኖ ሙሴ ታዛዥ በመሆን፣ እስራኤላውያን ቤተሰቦች የበኩር ልጆቻቸውን ከጥፋት ማትረፍ እንዲችሉ አስጠንቅቋል። የሰዎች ሕይወት አደጋ ላይ ነበር፤ ሙሴም ለወገኖቹ ፍቅር ነበረው። በመሆኑም መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው ሙሴ በፍጥነት “የእስራኤልን ሕዝብ አለቆች በሙሉ አስጠርቶ . . . ‘የፋሲካን በግ እረዱ’” አላቸው።—ዘፀ. 12:21
12. ይሖዋ፣ የትኛውን አስፈላጊ መልእክት እንድናውጅ አዝዞናል?
12 የይሖዋ ሕዝቦች በመላእክት በመታገዝ የሚከተለውን አስፈላጊ የሆነ መልእክት ለሰዎች እያወጁ ነው፦ “አምላክን ፍሩ፣ ክብርም ስጡት፤ ምክንያቱም እሱ ፍርድ የሚሰጥበት ሰዓት ደርሷል፤ በመሆኑም ሰማይን፣ ምድርን፣ ባሕርንና የውኃ ምንጮችን የሠራውን አምልኩ።” (ራእይ 14:7) ይህን መልእክት የምናውጅበት ጊዜ አሁን ነው። ሰዎች ታላቂቱ ባቢሎን ‘ከሚደርስባት መቅሰፍት ተካፋይ እንዳይሆኑ’ ከእሷ መውጣት እንዳለባቸው ማስጠንቀቅ ይኖርብናል። (ራእይ 18:4) ‘ሌሎች በጎችም’ ከቅቡዓን ክርስቲያኖች ጋር በመተባበር ከአምላክ የራቁ ሰዎችን ከእሱ ጋር ‘እንዲታረቁ’ እየለመኑ ነው።—ዮሐ. 10:16፤ 2 ቆሮ. 5:20
13. ምሥራቹን የመስበክ ፍላጎታችን እያደገ እንዲሄድ ምን ይረዳናል?
13 “ፍርድ የሚሰጥበት ሰዓት” እንደደረሰ እርግጠኞች ነን። ይሖዋ የስብከቱና ደቀ መዛሙርት የማድረጉ ሥራ አጣዳፊ መሆኑን መናገሩ የተጋነነ እንዳልሆነም እምነት አለን። ሐዋርያው ዮሐንስ “አራቱን የምድር ነፋሳት አጥብቀው” የያዙ “አራት መላእክት በአራቱ የምድር ማዕዘናት ቆመው” በራእይ ተመልክቶ ነበር። (ራእይ 7:1) እነዚህ መላእክት በዚህ ዓለም ላይ ታላቅ መከራን የሚያመጡትን የጥፋት ነፋሳት ለመልቀቅ በተጠንቀቅ ላይ እንደሆኑ በእምነት ዓይንህ ይታይሃል? እነዚህ መላእክት በእምነት ዓይንህ የሚታዩህ ከሆነ ምሥራቹን በሙሉ ልብ መስበክ ትችላለህ።
-
-
“የማይታየው” አምላክ ይታይሃል?መጠበቂያ ግንብ—2014 | ሚያዝያ 15
-
-
a ይሖዋ በግብፃውያን ላይ የፍርድ እርምጃ ለማስፈጸም የላከው መላእክትን እንደሆነ ከሁኔታው መረዳት ይቻላል።—መዝ. 78:49-51
-