-
የአንባብያን ጥያቄዎችመጠበቂያ ግንብ—2001 | ጥቅምት 1
-
-
ሐዋርያው ጳውሎስ በመጀመሪያው መቶ ዘመን ለነበሩት ዕብራውያን ክርስቲያኖች እንዲህ ሲል ጽፏል:- “የሰንበት ዕረፍት ለእግዚአብሔር ሕዝብ ቀርቶላቸዋል። ወደ ዕረፍቱ የገባ፣ እግዚአብሔር ከሥራው እንዳረፈ፣ እርሱ ደግሞ ከሥራው አርፎአልና። እንግዲህ . . . ወደዚያ ዕረፍት ለመግባት እንትጋ።”—ዕብራውያን 4:9-11
-
-
የአንባብያን ጥያቄዎችመጠበቂያ ግንብ—2001 | ጥቅምት 1
-
-
በዕብራውያን መጽሐፍ ላይ ወደሚገኘው የጳውሎስ ሐሳብ ስንመለስ “የሰንበት ዕረፍት ለእግዚአብሔር ሕዝብ ቀርቶላቸዋል” ብሎ መናገሩን የምናስተውል ከመሆኑም በላይ ክርስቲያን ባልንጀሮቹ “ወደዚያ ዕረፍት ለመግባት” ትጋት እንዲያሳዩ አሳስቧቸዋል። ይህም ማለት ጳውሎስ እነዚህን ቃላት በጻፈበት ወቅት 4, 000 ዓመታት ገደማ ያስቆጠረው አምላክ ያረፈበት ‘ሰባተኛው ቀን’ ገና አላበቃም ማለት ነው። ይህ ቀን “የሰንበት ጌታ” በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ የሺህ ዓመት ንግሥና ማብቂያ ላይ አምላክ ለሰው ልጆችና ለምድር ያለው ዓላማ ሙሉ በሙሉ ፍጻሜውን እስከሚያገኝበት ጊዜ ድረስ ይዘልቃል።—ማቴዎስ 12:8፤ ራእይ 20:1-6፤ 21:1-4
-
-
የአንባብያን ጥያቄዎችመጠበቂያ ግንብ—2001 | ጥቅምት 1
-
-
ጳውሎስ ስለ አምላክ ዕረፍትና አንድ ሰው ወደ ዕረፍቱ እንዴት ሊገባ እንደሚችል የሰጠው ማብራሪያ ለእምነታቸው ሲሉ ብዙ ስደትና ነቀፋ በጽናት ላሳለፉ በኢየሩሳሌም ለነበሩ ዕብራውያን ክርስቲያኖች የብርታት ምንጭ እንደሆነላቸው የተረጋገጠ ነው። (ሥራ 8:1፤ 12:1-5) በተመሳሳይ የጳውሎስ ቃላት በዛሬው ጊዜ ላሉ ክርስቲያኖች የብርታት ምንጭ ሊሆኑ ይችላሉ። አምላክ ጽድቅ በሰፈነበት መንግሥቱ አማካኝነት ምድርን ገነት ለማድረግ የገባው ቃል ፍጻሜውን የሚያገኝበት ጊዜ በጣም ቅርብ መሆኑን በመገንዘብ እኛም ከራሳችን ሥራ ማረፍና ወደ አምላክ ዕረፍት ለመግባት መትጋት ይኖርብናል።—ማቴዎስ 6:10, 33፤ 2 ጴጥሮስ 3:13
-