-
አንድን ቅዱስ ምሥጢር መፍታትራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
17. (ሀ) ኢየሱስ ስለ ስንዴና እንክርዳድ የሰጠው ምሳሌ ምን እንደሚሆን ተንብዮ ነበር? (ለ) በ1918 ምን ነገር ተፈጸመ? ይህስ እነማን እንዲወድቁና ማን እንዲሾም ምክንያት ሆነ?
17 ኢየሱስ ስለ ስንዴውና ስለ እንክርዳዱ በተናገረው ምሳሌ ሕዝበ ክርስትና የበላይ ሆና በምትገዛበት ዘመን ስለሚኖረው የጨለማ ጊዜ ተናግሮ ነበር። ይሁን እንጂ ክህደቱ በቆየባቸው መቶ ዘመናት ሁሉ ስንዴ መሰል የሆኑ ግለሰብ ክርስቲያኖች ወይም እውነተኛ ቅቡዓን መገኘት ነበረባቸው። (ማቴዎስ 13:24-29, 36-43) ስለዚህ የጌታ ቀን በጠባበት በጥቅምት ወር 1914 በምድር ላይ እውነተኛ ክርስቲያኖች ነበሩ። (ራእይ 1:10) ከሦስት ዓመት ተኩል በኋላ በ1918 ይሖዋ “የቃል ኪዳኑ መልእክተኛ” የሆነውን ኢየሱስን አስከትሎ ወደ መንፈሳዊ ቤተ መቅደሱ ለፍርድ” የመጣ ይመስላል። (ሚልክያስ 3:1፤ ማቴዎስ 13:47-50) ይህም ጌታው ሐሰተኛ ክርስቲያኖችን አስወግዶ በንብረቱ ሁሉ ላይ “ታማኝና ልባም ባሪያውን” የሚሾምበት ጊዜ ሆነ።—ማቴዎስ 7:22, 23፤ 24:45-47
18. በ1914 የምን “ሰዓት” ሆነ? ባሪያው ምን የሚያደርግበት ጊዜ ሆነ?
18 በተጨማሪም ለሰባቱ ጉባኤዎች ከተጻፈው መልእክት ለመረዳት እንደምንችለው ይህ ባሪያ ለዚህ የኢየሱስ መልእክት ልዩ ትኩረት የሚሰጥበት ጊዜ ደረሰ። ለምሳሌ ያህል ኢየሱስ ጉባኤውን ለመፍረድ እንደሚመጣ ተናግሮ ነበር። ይህም ፍርድ በ1918 ጀምሮአል። (ራእይ 2:5, 16, 22, 23፤ 3:3) የፊልድልፍያን ጉባኤ ‘በዓለም ሁሉ ላይ ሊመጣ ካለው የፍርድ ሰዓት እንደሚጠብቅ’ ተናግሮ ነበር። (ራእይ 3:10, 11) ይህ “የፍርድ ሰዓት” የመጣው በ1914 የጌታ ቀን እንደጀመረ ነው። ከጌታ ቀን በኋላ ክርስቲያኖች ሁሉ ለተቋቋመችው የአምላክ መንግሥት ባላቸው ታማኝነት ረገድ ይፈተናሉ።—ከማቴዎስ 24:3, 9-13 ጋር አወዳድር።
-
-
አንድን ቅዱስ ምሥጢር መፍታትራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ ሣጥን]
የፈተናና የፍርድ ጊዜ
ኢየሱስ እጩ ንጉሥ ሆኖ በዮርዳኖስ ወንዝ የተጠመቀውና የተቀባው በ29 እዘአ በጥቅምት ወር አካባቢ ነበር። ይህ ከሆነ ከሦስት ዓመት ተኩል በኋላ በ33 እዘአ በኢየሩሳሌም ወደነበረው ቤተ መቅደስ መጥቶ ቤተ መቅደሱን የወንበዴዎች ዋሻ ያደረጉትን ሰዎች አባረረ። ኢየሱስ ጥቅምት 1914 በሰማይ ከነገሠ በኋላ፣ ፍርድ ከአምላክ ቤት ስለሚጀምር ክርስቲያን ነን ይሉ የነበሩትን ሁሉ ለመመርመር እስኪመጣ ድረስ ሶስት ዓመት ተኩል ማለፉ ከዚህ ጋር ተመሳሳይነት ያለው ይመስላል። (ማቴዎስ 21:12, 13፤ 1 ጴጥሮስ 4:17) የይሖዋ ሕዝቦች ያካሂዱት የነበረው የመንግሥት የሥራ እንቅስቃሴ በ1918 መጀመሪያ ላይ ትልቅ ተቃውሞ ደርሶበት ነበር። በምድር በሙሉ የፈተና ጊዜ ሆኖ ነበር። ፍርሐት የነበራቸው ሁሉ በዚህ ጊዜ ተበጥረዋል። በግንቦት ወር 1918 የሕዝበ ክርስትና ቀሳውስት የመጠበቂያ ግንብ ማህበርን ባለ ሥልጣኖች አሳስረው ነበር። ከዘጠኝ ወር በኋላ ግን ከእሥራት ተፈቱ። በኋላም የቀረቡባቸው የሐሰት ክሶች ሁሉ ተነሱላቸው። ከ1919 ጀምሮ የአምላክ ሕዝቦች ድርጅት ከተፈተነና ከተጣራ በኋላ የሰው ልጆች ብቸኛ ተስፋ በክርስቶስ ኢየሱስ መሪነት የሚገዛው የአምላክ መንግሥት መሆኑን ለማወጅ በቅንዓት ወደፊት መገስገስ ጀመረ።—ሚልክያስ 3:1-3
ኢየሱስ ምርመራውን በ1918 ሲጀምር የሕዝበ ክርስትና ቀሳውስት የጥፋተኛነት ፍርድ እንደተፈረደባቸው ከሁኔታዎቹ መረዳት ይቻላል። በአምላክ ሕዝቦች ላይ ስደት በማነሳሳት ብቻ ሳይወሰኑ በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት እርስበርሳቸው ይዋጉ የነበሩትን መንግሥታት በመደገፍ በራሳቸው ላይ ከባድ የደም ዕዳ ጭነዋል። (ራእይ 18:21, 24) እነዚህ ቀሳውስት ተስፋቸውን የጣሉት ሰው ሠራሽ በሆነው በመንግሥታት ቃል ኪዳን ማኅበር ላይ ነበር። በ1919 ሕዝበ ክርስትና ከመላው የዓለም የሐሰት ሃይማኖት ግዛት ጋር ከአምላክ ሞገስ ውጭ በመሆን ወድቃለች።
-