-
የአምላክ የፍርድ ቀን—የሚያስገኘው አስደሳች ውጤት!ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
7, 8. (ሀ) የትኛው የመጽሐፍ ጥቅልል ነው የተከፈተው? ከዚያ በኋላ ምን ይሆናል? (ለ) ትንሣኤ የማይኖራቸው የትኞቹ ሰዎች ናቸው?
7 ዮሐንስ በመቀጠል እንዲህ ይላል:- “ሌላ መጽሐፍም ተከፈተ እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ነው፤ ሙታንም በመጻሕፍት ተጽፎ እንደ ነበረ እንደ ሥራቸው መጠን ተከፈሉ። ባሕርም በእርሱ ውስጥ ያሉትን ሙታን ሰጠ፣ ሞትና ሲኦልም በእነርሱ ዘንድ ያሉትን ሙታን ሰጡ፣ እያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን ተከፈለ።” (ራእይ 20:12ለ, 13) በጣም የሚያስደንቅ ትዕይንት ነው! ‘ባሕሩ፣ ሞትና ሲኦል’ እያንዳንዳቸው የየራሳቸው ድርሻ አላቸው። ቢሆንም እነዚህ ቃላት በተናጠል የሚወሰዱና የተለያየ ትርጉም ያላቸው አይደሉም።a ዮናስ በዓሣ ሆድ ውስጥ በነበረበትና በዚህም ምክንያት በባሕር መካከል በነበረበት ጊዜ በሲኦል ወይም በሔድስ ውስጥ እንደነበረ ተናግሮአል። (ዮናስ 2:3) አንድ ሰው በአዳማዊ ሞት መዳፍ ውስጥ የታሰረ ከሆነ በሲኦል ወይም በሔድስ ውስጥ ያለ ሊሆን ይችላል። እነዚህ ትንቢታዊ ቃላት ማንም ተረስቶ እንደማይቀር ዋስትና የሚሰጡ ናቸው።
-
-
የአምላክ የፍርድ ቀን—የሚያስገኘው አስደሳች ውጤት!ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
a ከባሕር ከሚነሱት ሙታን መካከል በኖህ ዘመን በጥፋት ውኃ የጠፉት ክፉ ሰዎች አይኖሩም። ይህ በእነርሱ ላይ የደረሰው ጥፋት በታላቁ መከራ በሚፈጸመው የይሖዋ ፍርድ በሚጠፉት ሰዎች ላይ እንደሚደርሰው ጥፋት የመጨረሻ ጥፋት ነው።—ማቴዎስ 25:41, 46፤ 2 ጴጥሮስ 3:5-7
-