-
የአምላክ መንግሥት ተወለደ!ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
22, 23. (ሀ) ዮሐንስ ዘንዶው ወደ ምድር ከተጣለ በኋላ የሆነውን ሲገልጽ ምን ምን ተናገረ? (ለ) ዘንዶው “ወንዱን ልጅ የወለደችውን ሴት” ሊያሳድድ የቻለው እንዴት ነው?
22 ሰይጣን ከሰማይ ከተጣለ ወዲህ በምድር ላይ የቀሩት የክርስቶስ ወንድሞች የሰይጣንን የቁጣ በትር ቀምሰዋል። ዮሐንስ እንዲህ በማለት ይነግረናል:- “ዘንዶውም ወደ ምድር እንደ ተጣለ ባየ ጊዜ ወንድ ልጅ የወለደችውን ሴት አሳደዳት። ከእባቡም ፊት ርቃ አንድ ዘመን፣ ዘመናትም፣ የዘመንም እኩሌታ ወደምትመገብበት ወደ ስፍራዋ ወደ በረሀ እንድትበር ለሴቲቱ ሁለት የታላቁ ንሥር ክንፎች ተሰጣት።”—ራእይ 12:13, 14
-
-
የአምላክ መንግሥት ተወለደ!ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
24. የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች እስራኤላውያን ከግብፅ በወጡ ጊዜ ያጋጠማቸውን የመሰለ ተሞክሮ ያጋጠማቸው እንዴት ነው?
24 የኢየሱስ ወንድሞች አንደኛው የዓለም ጦርነት ይካሄድባቸው በነበሩት ዓመታት ሁሉ በተቻላቸው መጠን የምስክርነቱን ሥራ በታማኝነት ሲያካሂዱ ቆይተው ነበር። ይህ ሁሉ ሥራ የተፈጸመው ከሰይጣንና ከግብረ አበሮቹ የተፋፋመ ተቃውሞ እየደረሰባቸው ነበር። በኋላ ግን የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ያከናውኑት የነበረው ሕዝባዊ ምሥክርነት ሙሉ በሙሉ እንደመቆም አለ። (ራእይ 11:7-10) ይህም የሆነው እሥራኤላውያን በግብፅ አገር ሳሉ የደረሰባቸውን የጭቆና ኑሮ የመሰለ ሁኔታ ባጋጠማቸው ጊዜ ነበር። ይሖዋ በሲና በረሐ እንደነበረው ወዳለ የእረፍት ቦታ በንስር ክንፍ ያመጣቸው በዚህ ጊዜ ነበር። (ዘጸአት 19:1-4) በተመሳሳይም ከ1918 እስከ 1919 ከነበረው የመራራ ስደት ጊዜ በኋላ ይሖዋ በሴቲቱ የተወከሉትን ምስክሮቹን ለእስራኤላውያን የእረፍት ሥፍራ የሆነላቸውን የሲና በረሐ ወደሚመስል መንፈሳዊ ሁኔታ አመጣቸው። ይህም የተደረገላቸው ለጸሎታቸው ምላሽ ለመስጠት ነው።—ከመዝሙር 55:6-9 ጋር አወዳድር።
25. (ሀ) ይሖዋ እስራኤላውያንን በምድረ በዳ መርቶ እንዳወጣ ሕዝቦቹን በ1919 መርቶ ያወጣው እንዴት ነው? (ለ) የዚህ ብሔር አባላት እነማን ናቸው? እንዴት ወዳለ ሁኔታስ መጥተዋል?
25 በምድረ በዳ ውስጥ ይሖዋ እስራኤላውያንን አንድ ብሔር አድርጎ በማቋቋም በመንፈሳዊም ሆነ በሥጋዊ የሚያስፈልጋቸውን ነገር ሁሉ እየሰጠ መርቶአቸዋል። በተመሳሳይም ከ1919 ጀምሮ ይሖዋ የሴቲቱን ዘሮች መንፈሳዊ ብሔር አድርጎ አውጥቶአቸዋል። ይሁን እንጂ ይህን ብሔር ከ1914 ጀምሮ በሰማይ ሆኖ ሲገዛ ከቆየው መሲሐዊ መንግሥት ጋር ማሳሳት አይገባንም። ይህ አዲስ ብሔር በ1919 ታላቅ ክብር ወዳለው መንፈሳዊ ርስት ከገቡት በዚህ ምድር ላይ ከሚገኙ የቅቡዓን ክርስቲያኖች ቀሪዎች የተውጣጣ ነው። በአሁኑ ጊዜ ‘በጊዜው የሚያስፈልጋቸውን ምግብ ስለሚያገኙ’ ከፊታቸው ለሚጠብቃቸው ሥራ የሚያስፈልጋቸውን ብርታትና ጥንካሬ አግኝተዋል።—ሉቃስ 12:42፤ ኢሳይያስ 66:8
26. (ሀ) በራእይ 12:6, 14 ላይ የተገለጸው ጊዜ ምን ያህል ርዝመት አለው? (ለ) የሦስት ተኩሉ ጊዜ ለምን ዓላማ የዋለ ነበር? የጀመረውና ያለቀውስ መቼ ነው?
26 ይህ የሴቲቱ ዘር የእረፍት ጊዜ የቆየው ለምን ያህል ጊዜ ነው? ለ1,260 ቀን እንደሆነ ራእይ 12:6 ይነግረናል። ራእይ 12:14 ደግሞ ዘመን፣ ዘመናትም፣ የዘመንም እኩሌታ ወይም በሌላ አነጋገር ሦስት ዓመት ተኩል እንደሆነ ይናገራል። ሁለቱም አነጋገሮች የሚያመለክቱት የሦስት ዓመት ተኩል ጊዜ ነው። ይህም ጊዜ በሰሜናዊው ንፍቀ ክበብ በሚገኙ አገሮች ከ1919 የጸደይ ወራት እስከ 1922 የበልግ ወራት የቆየው ጊዜ ነው። ይህ ጊዜ ተመልሰው ለተቋቋሙት የዮሐንስ ክፍል አባሎች የማገገሚያና እንደገና የመደራጃ ጊዜ ሆኖ ነበር።
-