ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ራእይ 1-3
‘ሥራህን አውቃለሁ’
“ሰባቱ ከዋክብት”፦ በመንፈስ የተቀቡ ሽማግሌዎች፣ በተዘዋዋሪ ደግሞ ሁሉም ሽማግሌዎች
‘በኢየሱስ ቀኝ እጅ’፦ ከዋክብቱ በኢየሱስ ሙሉ ቁጥጥር፣ ሥልጣንና አመራር ሥር ናቸው። የሽማግሌዎች አካል አባል የሆነ ሰው ማስተካከያ ካስፈለገው ኢየሱስ በራሱ ጊዜና መንገድ ይህ ወንድም እርማት እንዲያገኝ ያደርጋል
“ሰባቱ የወርቅ መቅረዞች”፦ የክርስቲያን ጉባኤዎች። በማደሪያ ድንኳኑ ውስጥ የነበረው መቅረዝ ቃል በቃል ብርሃን ይፈነጥቅ እንደነበር ሁሉ የክርስቲያን ጉባኤዎችም መንፈሳዊ ብርሃን ይፈነጥቃሉ። (ማቴ 5:14) ኢየሱስ በመቅረዞቹ ‘መካከል እንደሚመላለስ’ መገለጹ የሁሉንም ጉባኤዎች እንቅስቃሴ በበላይነት እንደሚከታተል የሚያመለክት ነው