-
የሐሰት ሃይማኖቶች የአምላክን ስም ያሰደቡት እንዴት ነው?ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
2. የሐሰት ሃይማኖቶች በድርጊታቸው አምላክን የሚያሰድቡት እንዴት ነው?
የሐሰት ሃይማኖት መሪዎች ሰዎችን የሚይዙበት መንገድ ይሖዋ ሰዎችን ከሚይዝበት መንገድ ፈጽሞ የተለየ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ የሐሰት ሃይማኖት ‘ኃጢአት እስከ ሰማይ ድረስ እንደተቆለለ’ ይናገራል። (ራእይ 18:5) በመቶዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት፣ ሃይማኖቶች ፖለቲካ ውስጥ ሲገቡና ጦርነቶችን ሲደግፉ ቆይተዋል፤ በተጨማሪም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ፣ ስፍር ቁጥር ለሌላቸው ሰዎች ሞት ምክንያት ሆነዋል። አንዳንድ የሃይማኖት መሪዎች የተንደላቀቀ ሕይወት ለመኖር ሲሉ ተከታዮቻቸውን ገንዘብ እንዲያመጡ ይጠይቃሉ። እንዲህ ያሉት ድርጊቶች እነዚህ ሃይማኖቶች አምላክን ሊወክሉ ቀርቶ ጨርሶ እንደማያውቁት ያሳያሉ።—1 ዮሐንስ 4:8ን አንብብ።
-
-
ምንጊዜም ለይሖዋ ታማኝ ሁንለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
ሉቃስ 4:8ን እና ራእይ 18:4, 5ን አንብቡ፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
ስሜ አሁንም በሐሰት ሃይማኖት አባላት ስም ዝርዝር ውስጥ ይገኛል?
ከሌላ ሃይማኖት ጋር ንክኪ ያለው ድርጅት አባል ነኝ?
የምሠራው ሥራ በሆነ መንገድ ለሐሰት ሃይማኖት ድጋፍ የሚሰጥ ነው?
በሕይወቴ ውስጥ ከሐሰት ሃይማኖት ጋር ሊያነካኩኝ የሚችሉ ሌሎች አቅጣጫዎች ይኖሩ ይሆን?
ከእነዚህ ጥያቄዎች መካከል ለአንዱም እንኳ ‘አዎ’ የሚል መልስ ከሰጠሁ ምን ለውጥ ማድረግ ይኖርብኛል?
በማንኛውም ሁኔታ ሥር ሕሊናህን የማይረብሽና ለይሖዋ ያለህን ታማኝነት የሚያሳይ ውሳኔ አድርግ።
አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ፦ “ለእውነት ጥብቅና መቆም እንድችል ከሃዲዎች ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ምን እንደሚሉ ማወቅ አለብኝ።”
-