-
መለኮታዊው ስም—አስፈላጊነቱና ትርጉሙትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
-
-
የአምላክን ስም የማይጠቀሙ ከሆነ በጣም አስደናቂ የሆነውን የስሙን ትርጉም ሳይገነዘቡ ይቀራሉ። መለኮታዊው ስም ትርጉሙ ምንድን ነው?
ይሖዋ ራሱ የስሙን ትርጉም ታማኝ ለሆነው አገልጋዩ ለሙሴ ገልጾለታል። ሙሴ ስለ አምላክ ስም በጠየቀ ጊዜ ይሖዋ “መሆን የሚያስፈልገኝን ሁሉ እሆናለሁ” በማለት መልስ ሰጥቶታል። (ዘፀአት 3:14 NW) የሮዘርሃም ትርጉም እነዚህን ቃላት “መሆን የምሻውን ሁሉ እሆናለሁ” ሲል ተርጉሟቸዋል። ስለዚህ ይሖዋ ዓላማዎቹን ዳር ለማድረስ መሆን የሚያስፈልገውን ሁሉ መሆን ይችላል።
መሆን የምትፈልገውን ሁሉ መሆን ትችላለህ እንበል። ለጓደኞችህ ምን ታደርግላቸው ነበር? ከጓደኞችህ መካከል አንዱ በጣም ቢታመም የተዋጣለት ዶክተር በመሆን ልትፈውሰው ትችላለህ። ሌላው ጓደኛህ የገንዘብ ኪሳራ ቢደርስበት ወዲያውኑ ባለጸጋ ሰው ሆነህ ገንዘብ በመለገስ ከደረሰበት ኪሳራ ልትታደገው ትችላለህ። ዳሩ ምን ያደርጋል ይህን ሁሉ ለመሆን አቅምህ አይፈቅድም። ሁላችንም ብንሆን ያለን አቅም ውስን ነው። መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናት ይሖዋ ቃል የገባቸውን ነገሮች ለመፈጸም መሆን የሚያስፈልገውን ሁሉ እንዴት መሆን እንደሚችል ስታውቅ በጣም ትገረማለህ። ከዚህም በተጨማሪ ይሖዋ ኃይሉን እሱን ለሚወዱት ሰዎች ጥቅም ማዋል በጣም ያስደስተዋል። (2 ዜና መዋዕል 16:9) ስሙን የማያውቁ ሰዎች እነዚህን አስደሳች የሆኑ የይሖዋ ባሕርያት ገጽታዎች ሳይረዱ ይቀራሉ።
በግልጽ መረዳት እንደሚቻለው ይሖዋ የሚለው ስም ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሊወጣ አይገባውም። የስሙን ትርጉም ማወቃችንና ስሙን በአምልኳችን ውስጥ በሚገባ መጠቀማችን ሰማያዊ አባታችን ወደሆነው ወደ ይሖዋ ይበልጥ እንድንቀርብ በእጅጉ ይረዳናል።a
-
-
የዳንኤል ትንቢት መሲሑ የሚመጣበትን ጊዜ አስቀድሞ የተናገረው እንዴት ነው?ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
-
-
ተጨማሪ ክፍል
የዳንኤል ትንቢት መሲሑ የሚመጣበትን ጊዜ አስቀድሞ የተናገረው እንዴት ነው?
ነቢዩ ዳንኤል የኖረው ኢየሱስ ከመወለዱ ከ500 ከሚበልጡ ዓመታት በፊት ነው። ያም ሆኖ ይሖዋ፣ ኢየሱስ መሲሕ ወይም ክርስቶስ ሆኖ የሚቀባበትን ወይም የሚሾምበትን ጊዜ በትክክል ለይቶ ለማወቅ የሚያስችል መረጃ ለዳንኤል ገልጦለት ነበር። ዳንኤል “ይህንን ዕወቅ፤ አስተውለውም፤ ኢየሩሳሌምን ለማደስና ለመጠገን ዐዋጁ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ፣ ገዥው መሲሕ እስከሚመጣበት ጊዜ ድረስ፣ ሰባት ሱባዔና ሥልሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል” ተብሎ ተነግሮት ነበር።—ዳንኤል 9:25
መሲሑ የሚመጣበትን ጊዜ ለይተን ለማወቅ በቅድሚያ ወደ መሲሑ የሚያደርሰን ዘመን መቼ እንደጀመረ ማወቅ ያስፈልገናል። በትንቢቱ መሠረት ይህ ዘመን የሚጀምረው “ኢየሩሳሌምን ለማደስና ለመጠገን ዐዋጁ” በሚወጣበት ጊዜ ነው። ‘ዐዋጁ የወጣው’ መቼ ነው? የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊ የሆነው ነህምያ እንደገለጸው የኢየሩሳሌም ግንቦች ዳግመኛ እንዲገነቡ ዐዋጅ የወጣው “በንጉሡ በአርጤክስስ ዘመነ መንግሥት በሃያኛው ዓመት” ነው። (ነህምያ 2:1, 5-8) የአርጤክስስ የግዛት ዘመን የጀመረው በ475 ከክርስቶስ ልደት በፊት እንደሆነ ታሪክ ጸሐፊዎች አረጋግጠዋል። ስለዚህ 20ኛው የግዛት ዓመቱ 455 ከክርስቶስ ልደት በፊት ነው። አሁን ዳንኤል መሲሑን አስመልክቶ የተናገረው ትንቢት መፈጸም የጀመረው በ455 ከክርስቶስ ልደት በፊት እንደሆነ ተገንዝበናል።
ዳንኤል “ገዥው መሲሕ” እስከሚመጣበት ወቅት ድረስ ያለው የጊዜ ርዝማኔ ምን ያህል እንደሆነ አመልክቷል። ትንቢቱ “ሰባት ሱባዔና ሥልሳ ሁለት ሱባዔ” በድምሩ 69 ሱባዔ እንደሆነ ይገልጻል። ይህ ጊዜ ምን ያህል ርዝማኔ አለው? በርከት ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች እነዚህ ሱባዔዎች ሰባት ቀናትን ያቀፉ ሳምንታት ሳይሆኑ የዓመታት ሳምንታት እንደሆኑ ይገልጻሉ። ስለዚህ እያንዳንዱ ሳምንት ሰባት ዓመታትን ይወክላል ማለት ነው። ይህ የዓመታት ሳምንታት ወይም ዓመታትን በሰባት ዓመት የመክፈል ጽንሰ ሐሳብ በጥንት ዘመን ለነበሩት አይሁዶች አዲስ አልነበረም። ለምሳሌ ያህል በየሰባት ዓመቱ የሰንበት ዓመት ያከብሩ ነበር። (ዘፀአት 23:10, 11) ስለዚህ በትንቢት የተነገሩት 69 ሳምንታት እያንዳንዳቸው 7 ዓመታትን ያቀፉ 69 የዓመታት ክፍሎች ወይም በድምሩ 483 ዓመታት ናቸው።
አሁን የቀረን ነገር መቁጠር ብቻ ነው። ከ455 ከክርስቶስ ልደት በፊት ተነስተን 483 ዓመታት ብንቆጥር 29 ከክርስቶስ ልደት በኋላ ላይ እንደርሳለን። ይህ ኢየሱስ የተጠመቀበትና መሲሕ የሆነበት ዓመት ነው!a (ሉቃስ 3:1, 2, 21, 22) ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት የተፈጸመበት ሁኔታ እጅግ አያስደንቅም?
a ከ455 ከክርስቶስ ልደት በፊት እስከ 1 ከክርስቶስ ልደት በፊት ድረስ 454 ዓመታት አሉ። ከ1 ከክርስቶስ ልደት በፊት እስከ 1 ከክርስቶስ ልደት በኋላ ድረስ አንድ ዓመት ነው። (ዜሮ የሚባል ዓመት የለም።) ከ1 ከክርስቶስ ልደት በኋላ እስከ 29 ከክርስቶስ ልደት በኋላ 28 ዓመት ነው። እነዚህን ሦስት አኃዞች ስንደምር 483 ዓመታት ይሆናሉ። ኢየሱስ ‘የተገደለው’ በ33 ከክርስቶስ ልደት በኋላ ማለትም በ70ኛው የዓመታት ሳምንት ነው። (ዳንኤል 9:24, 26) የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል! የተባለውን መጽሐፍ ምዕራፍ 11 እና ቅዱሳን ጽሑፎችን ጠለቅ ብሎ ማስተዋል (እንግሊዝኛ) የተባለውን መጽሐፍ ጥራዝ 2 ከገጽ 899-901 ተመልከት። ሁለቱም ጽሑፎች የተዘጋጁት በይሖዋ ምሥክሮች ነው።
-
-
ኢየሱስ ክርስቶስ—አስቀድሞ የተነገረለት መሲሕትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
-
-
ተጨማሪ ክፍል
ኢየሱስ ክርስቶስ—አስቀድሞ የተነገረለት መሲሕ
ይሖዋ አምላክ መሲሑን ለይተን ማወቅ እንድንችል ለመርዳት በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ነቢያት የሰውን ዘር ነፃ እንደሚያወጣ የተነገረለት ይህ መሲሕ ስለሚወለድበት ሁኔታ፣ ስለ አገልግሎቱና ስለ አሟሟቱ ዝርዝር መረጃዎችን እንዲሰጡ በመንፈሱ አነሳስቷቸዋል። እነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች
-