መዝሙር 11
የይሖዋን ልብ ማስደሰት
በወረቀት የሚታተመው
1. አምላክ ቃል ገባን፣ ወሰንን፤
ለመፈጸም ፈቃድህን።
ስንመራ በጥበብህ፣
በኛ ደስ ይሰኛል ልብህ።
2. ምድር ያለው ታማኝ ባሪያህ፣
ያውጃል ታላቅ ስምህን፤
በጊዜው ይመግበናል፤
ለሥራህ ያስታጥቀናል።
3. ’ባክህ ስጠን መንፈስህን፤
እንድንኖር ታማኝ ሆነን፤
ከልብ እንድናወድስህ፣
ሁሌም ደስ እንድናሰኝህ።
(በተጨማሪም ማቴ. 24:45-47ን፣ ሉቃስ 11:13ን እና ሉቃስ 22:42ን ተመልከት።)