መዝሙር 87
አንድ ሆነናል
በወረቀት የሚታተመው
1. ያጥንቶቼ አጥንት ናት፤
አምላክ የሰጠኝ፣ የኔ ’ምላት።
ሥጋዋም አንድ ከሥጋዬ፤
ሆነችኝ አጋሬ።
አንድ ሆነናል፤
’ናሳካለን ይሖዋ ’ሚፈልግብንን።
ወንድ ከሴት ተጣምረናል፤
ቤተሰብ ሆነናል።
ይሖዋን ’ናገለግላለን።
ልክ እንደ እሱ
ጽኑ ፍቅር ይኑረን።
መሐላችን ይሳካልን፤
የደስታ ጊዜ ይሁንልን።
ይሖዋ በኛ ይከበር፤
አንቺም ሁኚ የኔ ፍቅር።
(በተጨማሪም ዘፍ. 29:18ን፣ መክ. 4:9, 10ን እና 1 ቆሮ. 13:8ን ተመልከት።)