መዝሙር 55
አትፍሯቸው!
በወረቀት የሚታተመው
1. ሕዝቦቼ ወደፊት ግፉ፤
ምሥራቹን አስፋፉ።
አትፍሩ ጠላቶችን።
አሳውቁ ቅኖችን፣
ልጄ ክርስቶስ መንገሡን፣
ጠላቱን መወርወሩን፤
በቅርቡም ሰይጣንን ያስራል፤
ምርኮኞችን ያስፈታል።
(አዝማች)
አትፍሩ የኔ ወዳጆች፤
ቢዝቱ ’ንኳ ጠላቶች።
’ጠብቃለሁ ታማኞቼን፤
ልክ እንደ ዓይኔ ብሌን።
2. ጠላቶቻችሁ ቢበዙም፣
ቢዝቱ፣ ቢሳደቡም፣
ለመሸንገል ቢጥሩ፣
ለማሳት ቢሞክሩ፣
ሕዝቦቼ አትሸበሩ፤
ቢቃወሙም አትፍሩ።
ድል እስኪገኝ ባርማጌዶን፣
አልጥልም ታማኞችን።
(አዝማች)
አትፍሩ የኔ ወዳጆች፤
ቢዝቱ ’ንኳ ጠላቶች።
’ጠብቃለሁ ታማኞቼን፤
ልክ እንደ ዓይኔ ብሌን።
3. አትስጉ አልተዋችሁም፤
ጋሻችሁ ነኝ አሁንም።
በስደት ብትሞቱም፣
ሞታችሁ አትቀሩም።
ነፍስን መግደል ’ማይችሉትን
ፈጽሞ አትፍሯቸው።
ባቋማችሁ ከጸናችሁ
ሕይወት ታገኛላችሁ!
(አዝማች)
አትፍሩ የኔ ወዳጆች፤
ቢዝቱ ’ንኳ ጠላቶች።
’ጠብቃለሁ ታማኞቼን፤
ልክ እንደ ዓይኔ ብሌን።
(በተጨማሪም ዘዳ. 32:10ን፣ ነህ. 4:14ን፣ መዝ. 59:1ን እና 83:2, 3ን ተመልከት።)