ሣጥን 9መ
ስለ ግዞትና ስለ መልሶ መቋቋም የሚገልጹ ትንቢቶች
በወረቀት የሚታተመው
ከአይሁዳውያን የባቢሎን ግዞት ጋር በተያያዘ የተነገሩ በርካታ ትንቢቶች ከረጅም ዘመን በኋላ የክርስቲያን ጉባኤ በታላቂቱ ባቢሎን በምርኮ በተያዘበት ወቅት በላቀ ሁኔታ ፍጻሜያቸውን አግኝተዋል። አንዳንድ ምሳሌዎችን እንመልከት።
1. ማስጠንቀቂያዎች |
2. ግዞት |
3. መልሶ መቋቋም |
|
---|---|---|---|
የመጀመሪያው ፍጻሜ |
ከ607 ዓ.ዓ. በፊት—ኢሳይያስ፣ ኤርምያስና ሕዝቅኤል የይሖዋን ሕዝቦች ቢያስጠነቅቁም ክህደት መስፋፋቱን ቀጠለ |
607 ዓ.ዓ.—ኢየሩሳሌም ጠፋች፤ የአምላክ ሕዝቦች በግዞት ወደ ባቢሎን ተወሰዱ |
537 ዓ.ዓ. እና ከዚያ በኋላ—ታማኝ አይሁዳውያን ቀሪዎች ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው ቤተ መቅደሱን ገነቡ፤ እንዲሁም እንደ ቀድሞው ንጹሕ አምልኮ ማቅረብ ጀመሩ |
የላቀ ፍጻሜ |
በመጀመሪያው መቶ ዘመን ዓ.ም.—ኢየሱስ፣ ጳውሎስና ዮሐንስ ለጉባኤው ማስጠንቀቂያ ሰጥተው ነበር፤ ነገር ግን ክህደት መስፋፋቱን ቀጠለ |
ከሁለተኛው መቶ ዘመን ዓ.ም. ጀምሮ—እውነተኛ ክርስቲያኖች በታላቂቱ ባቢሎን ግዞት ሥር ወደቁ |
1919 ዓ.ም. እና ከዚያ በኋላ—ታማኝ ቅቡዓን ክርስቲያኖች በኢየሱስ ንግሥና ሥር ከመንፈሳዊ ምርኮ ነፃ የወጡ ሲሆን ንጹሕ አምልኮ መልሶ ሲቋቋም ተመልክተዋል |