ጥናት 18
ግንዛቤ የሚያሰፋ
1 ቆሮንቶስ 9:19-23
ፍሬ ሐሳብ፦ አድማጮችህ ርዕሰ ጉዳዩን እንዲያስቡበት ብሎም ጠቃሚ ትምህርት እንዳገኙ እንዲሰማቸው በሚያደርግ መንገድ ትምህርቱን ለማቅረብ ጥረት አድርግ።
ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?
አድማጮችህ ስለ ጉዳዩ ያላቸውን እውቀት ግምት ውስጥ አስገባ። ከዚህ በፊት የሚያውቋቸውን ነገሮች እንዲሁ ከመድገም ይልቅ ርዕሰ ጉዳዩን ከሌላ አቅጣጫ እንዲመለከቱት እርዳቸው።
ምርምር አድርግ እንዲሁም አሰላስል። ቁልፍ የሆኑ ነጥቦችን ለማስረዳት፣ አድማጮች ብዙም የማያውቋቸውን መረጃዎች ወይም ወቅታዊ ሁኔታዎች ጥቀስ። ስለምታቀርበው ትምህርት እንዲሁም በርዕሰ ጉዳዩና በምትጠቅሳቸው መረጃዎች መካከል ስላለው ዝምድና በጥሞና አስብ።
የትምህርቱን ጠቀሜታ አጉላ። ከመጽሐፍ ቅዱስ የምትጠቅሳቸው ሐሳቦች አድማጮችን በዕለታዊ ሕይወታቸው እንዴት ሊጠቅሟቸው እንደሚችሉ ግለጽ። ከአድማጮችህ ሕይወት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሁኔታዎች፣ አመለካከቶችና ድርጊቶች እንደ ምሳሌ በመጥቀስ ትምህርቱን አብራራ።