ሐሙስ፣ ሐምሌ 2
ወልድ ነፃ ካወጣችሁ፣ በእርግጥ ነፃ ትሆናላችሁ።—ዮሐ. 8:36
ኢየሱስ እንዲህ ሲል ከሁሉ ከከፋው ባርነትና ጭቆና ይኸውም “የኃጢአት ባሪያ” ከመሆን ነፃ ስለመውጣት መናገሩ ነበር። (ዮሐ. 8:34) ኃጢአት፣ መጥፎ ነገር መፈጸም እንዲቀናን የሚያደርገን ከመሆኑም ሌላ ትክክል እንደሆነ የምናውቀውን ነገር እንዳናደርግ አሊያም የአቅማችንን ያህል እንዳንሠራ ያግደናል። በመሆኑም የኃጢአት ባሪያዎች ነን ማለት ይቻላል፤ ይህ ደግሞ ብስጭት፣ ሥቃይ፣ መከራ በመጨረሻም ሞት ያስከትልብናል። (ሮም 6:23) የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን የነበራቸው ዓይነት እውነተኛ ነፃነት ማግኘት የምንችለው እንደ ካቴና ጠፍሮ ከያዘን ከኃጢአት ነፃ ስንወጣ ብቻ ነው። ኢየሱስ “ቃሌን ጠብቃችሁ ብትኖሩ” ማለቱ፣ እሱ ነፃ እንዲያወጣን ከፈለግን ልናሟላቸው የሚገቡ ብቃቶች እንዳሉ ይጠቁማል። (ዮሐ. 8:34) ሕይወታችንን ለይሖዋ የወሰንን ክርስቲያኖች እንደመሆናችን መጠን ራሳችንን ክደናል፤ እንዲሁም የክርስቶስ ደቀ መዝሙር መሆን ከሚያስከትላቸው ገደቦች ሳንወጣ ለመኖር መርጠናል። (ማቴ. 16:24) ከኢየሱስ ቤዛዊ መሥዋዕት ሙሉ በሙሉ ተጠቃሚ ስንሆን እሱ ቃል በገባው መሠረት እውነተኛ ነፃነት እናገኛለን። w18.04 7 አን. 14-16