ረቡዕ፣ ሐምሌ 8
ጎበዝ፣ አንተ ጥሩና ታማኝ ባሪያ! በጥቂት ነገሮች ታማኝ ሆነህ ተገኝተሃል። ስለዚህ በብዙ ነገሮች ላይ እሾምሃለሁ። ወደ ጌታህ ደስታ ግባ።—ማቴ. 25:21
የይሖዋ ልጅ ወደ ምድር ከመምጣቱና ሌሎችን በማበረታታት ረገድ ፍጹም ምሳሌ ከመተዉ በፊትም እንኳ የይሖዋ ታማኝ አገልጋዮች ማበረታቻ የመስጠትን አስፈላጊነት ተገንዝበው ነበር። አሦራውያን ዛቻ በሰነዘሩበት ወቅት ሕዝቅያስ የጦር አለቆቹንና የይሁዳን ሕዝብ ሰብስቦ አበረታቷል። “ሕዝቡም [እሱ] በተናገረው ቃል ተበረታታ።” (2 ዜና 32:6-8) ኢዮብ እሱ ራሱ ማጽናኛ ያስፈልገው የነበረ ቢሆንም ‘የሚያስጨንቁ አጽናኞች’ ለነበሩት ሦስት ጓደኞቹ ሌሎችን ማበረታታት የሚቻልበትን መንገድ በተመለከተ ጠቃሚ ትምህርት ሰጥቷቸዋል። እሱ በእነሱ ቦታ ቢሆን ኖሮ ‘በአፉ ቃል ያበረታቸውና በከንፈሮቹ ማጽናኛ ያሳርፋቸው እንደነበር’ ገልጾላቸዋል። (ኢዮብ 16:1-5) በመጨረሻም ኢዮብ ከኤሊሁ እንዲሁም ከይሖዋ ከራሱ ማበረታቻ አግኝቷል።—ኢዮብ 33:24, 25፤ 36:1, 11፤ 42:7, 10፤ w18.04 16 አን. 6፤ 17 አን. 8-9