ኢዮብ
29 ኢዮብ ንግግሩን* በመቀጠል እንዲህ አለ፦
2 “የቀድሞዎቹን ወራት፣
አምላክ ለእኔ ጥበቃ ያደርግ የነበረበትን ዘመን ተመኘሁ!
3 ያን ጊዜ መብራቱን በራሴ ላይ ያበራ፣
በእሱም ብርሃን፣ በጨለማ ውስጥ እሄድ ነበር፤+
4 ያኔ የወጣትነት ብርታት ነበረኝ፤
አምላክ የቅርብ ወዳጄ ሆኖ በድንኳኔ ይገኝ ነበር፤+
5 ሁሉን ቻይ አምላክ ከእኔ ጋር ነበር፤
ልጆቼም* በዙሪያዬ ነበሩ፤
6 መንገዴ በቅቤ የራሰ ነበር፤
ዓለቱም ዘይት ያንዶለዱልልኝ ነበር።+
9 መኳንንት ከመናገር ይቆጠቡ፣
እጃቸውንም በአፋቸው ላይ ይጭኑ ነበር።
10 የታላላቆቹ ሰዎች ድምፅ አይሰማም ነበር፤
ምላሳቸውም ከላንቃቸው ጋር ይጣበቅ ነበር።
11 ስናገር የሰማ ሁሉ ያሞግሰኝ፣
ያዩኝ ሰዎችም ይመሠክሩልኝ ነበር።
14 ጽድቅን እንደ ልብስ ለበስኩ፤
የፍትሕ አቋሜ እንደ ቀሚስና* እንደ ጥምጥም ሆነልኝ።
15 ለዓይነ ስውሩ ዓይን፣
ለአንካሳውም እግር ነበርኩ።
17 የክፉ አድራጊውን መንጋጋ እሰብር፣+
አድኖ የያዘውንም ከጥርሱ አስጥል ነበር።
19 ሥሮቼ ወደ ውኃ ይዘረጋሉ፤
ጠልም ሌሊቱን ሙሉ በቅርንጫፎቼ ላይ ያድራል።
20 ክብሬ ሁልጊዜ ይታደሳል፤
በእጄም ያለው ደጋን ደጋግሞ ይወነጭፋል።’
21 ሰዎች በጉጉት ያዳምጡኝ፣
ምክሬንም ጸጥ ብለው ይጠባበቁ ነበር።+
22 እኔ ከተናገርኩ በኋላ የሚጨምሩት ነገር አልነበረም፤
ቃሌም በጆሯቸው ይንቆረቆር* ነበር።
23 ዝናብ እንደሚጠባበቁ ሰዎች እኔን ተጠባበቁ፤
ቃሌንም እንደ በልግ ዝናብ+ ጠጡ።