ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር።
120 በተጨነቅኩ ጊዜ ይሖዋን ተጣራሁ፤+
እሱም መለሰልኝ።+
2 ይሖዋ ሆይ፣ ከሐሰተኛ ከንፈር፣
ደግሞም ከአታላይ አንደበት ታደገኝ።
3 አንተ አታላይ አንደበት፣
አምላክ ምን ያደርግህ ይሆን? እንዴትስ ይቀጣህ ይሆን?+
4 ሹል በሆኑ የተዋጊ ፍላጻዎችና+
በክትክታ እንጨት ፍም+ ይቀጣሃል።
5 በመሼቅ+ የባዕድ አገር ሰው ሆኜ ስለኖርኩ ወዮልኝ!
በቄዳር+ ድንኳኖች መካከል ኖሬአለሁ።
6 ሰላም ከሚጠሉ ሰዎች ጋር
ለረጅም ጊዜ ኖሬአለሁ።+
7 እኔ ለሰላም ቆሜአለሁ፤
እነሱ ግን በተናገርኩ ቁጥር ለጦርነት ይነሳሉ።