ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር።
129 “ከወጣትነቴ ጀምሮ ሁልጊዜ ያጠቁኝ ነበር”፤+
እስራኤል እንዲህ ይበል፦
2 “ከወጣትነቴ ጀምሮ ሁልጊዜ ያጠቁኝ ነበር፤+
ሆኖም ሊያሸንፉኝ አልቻሉም።+
3 አራሾች ጀርባዬን አረሱት፤+
ትልማቸውንም አስረዘሙት።”
4 ይሖዋ ግን ጻድቅ ነው፤+
የክፉዎችን ገመድ በጣጥሷል።+
5 ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ፣
ኀፍረት ይከናነባሉ፤ ተዋርደውም ወደኋላቸው ይመለሳሉ።+
6 ከመነቀሉ በፊት እንደሚጠወልግ፣
በጣሪያ ላይ እንደበቀለ ሣር ይሆናሉ፤
7 እንዲህ ዓይነቱ ሣር የአጫጁን እጅ፣
ነዶ የሚሰበስበውንም ሰው ክንዶች ሊሞላ አይችልም።
8 በዚያ የሚያልፉ ሰዎች
“የይሖዋ በረከት በእናንተ ላይ ይሁን፤
በይሖዋ ስም እንባርካችኋለን” አይሉም።