መዝሙር
የዳዊት መዝሙር።
28 ዓለቴ ይሖዋ ሆይ፣ ሁልጊዜ ወደ አንተ እጣራለሁ፤+
አንተም ጆሮ አትንፈገኝ።
2 ወደ መቅደስህ ውስጠኛ ክፍል እጆቼን አንስቼ፣
እርዳታ ለማግኘት ወደ አንተ በምጮኽበት ጊዜ ልመናዬን ስማ።+
4 ለሠሩት ሥራ፣
እንደ ክፉ ልማዳቸው ክፈላቸው።+
ለእጃቸው ሥራ መልሰህ ክፈላቸው፤
እንዳደረጉትም መልስላቸው።+
5 ይሖዋ ላከናወናቸው ነገሮች፣
ለእጆቹም ሥራ ትኩረት አይሰጡምና።+
እሱ ያፈርሳቸዋል፤ ደግሞም አይገነባቸውም።
6 እርዳታ ለማግኘት ያቀረብኩትን ልመና ስለሰማ
ይሖዋ የተመሰገነ ይሁን።
ከእሱ እርዳታ ስላገኘሁ ልቤ ሐሴት ያደርጋል፤
በመዝሙሬም አወድሰዋለሁ።
8 ይሖዋ ለሕዝቡ ብርታት ነው፤
ለቀባው ታላቅ መዳን የሚያስገኝ መሸሸጊያ ነው።+
9 ሕዝብህን አድን፤ ርስትህንም ባርክ።+
ለዘላለም እረኛ ሁናቸው፤ በክንድህም ተሸከማቸው።+