የአሳፍ+ ማህሌት።
82 አምላክ በመለኮታዊ ጉባኤ መካከል ይሰየማል፤+
በአማልክት መካከል ይፈርዳል፦+
2 “ፍትሕ የምታዛቡት እስከ መቼ ነው?+
ለክፉዎችስ የምታዳሉት እስከ መቼ ነው?+ (ሴላ)
3 ለችግረኛውና አባት ለሌለው ተሟገቱ።+
ረዳት የሌለውና ምስኪኑ ፍትሕ እንዲያገኝ አድርጉ።+
4 ችግረኛውንና ድሃውን ታደጉ፤
ከክፉዎችም እጅ አድኗቸው።”
5 ፈራጆቹ ምንም አያውቁም፤ ደግሞም አያስተውሉም፤+
በጨለማ ውስጥ ይመላለሳሉ፤
የምድር መሠረቶች ሁሉ ተናግተዋል።+
6 “እኔም እንዲህ አልኩ፦ ‘እናንተ አማልክት ናችሁ፤+
ሁላችሁም የልዑሉ አምላክ ልጆች ናችሁ።
7 ይሁንና እናንተም ሰው እንደሚሞተው ትሞታላችሁ፤+
ደግሞም እንደ ማንኛውም ገዢ ትወድቃላችሁ!’”+
8 አምላክ ሆይ፣ ተነስ፤ በምድርም ላይ ፍረድ፤+
ብሔራት ሁሉ የአንተ ናቸውና።