መዝሙር
መላዋ ምድር ለይሖዋ ትዘምር!+
2 ለይሖዋ ዘምሩ፤ ስሙንም አወድሱ።
የማዳኑን ምሥራች በየቀኑ አውጁ።+
4 ይሖዋ ታላቅ ነው፤ ደግሞም እጅግ ሊወደስ ይገባዋል።
ከሌሎች አማልክት ሁሉ በላይ እጅግ የሚፈራ ነው።
7 እናንተ የሕዝብ ነገዶች፣ ለይሖዋ የሚገባውን ስጡ፤
ከክብሩና ከብርታቱ የተነሳ ለይሖዋ የሚገባውን ስጡ።+
10 በብሔራት መካከል እንዲህ ብላችሁ አስታውቁ፦ “ይሖዋ ነገሠ!+
ምድር* በጽኑ ተመሥርታለች፤ ከቦታዋ ልትንቀሳቀስ አትችልም።*
11 ሰማያት ሐሴት ያድርጉ፤ ምድርም ደስ ይበላት፤
ባሕሩና በውስጡ ያለው ነገር ሁሉ የነጎድጓድ ድምፅ ያሰማ፤+
12 መስኩና በላዩ ላይ ያለው ሁሉ ሐሴት ያድርግ።+
የዱር ዛፎችም ሁሉ በይሖዋ ፊት እልል ይበሉ።+
13 እሱ እየመጣ ነውና፤*
በምድር ላይ ለመፍረድ እየመጣ ነው።