ምሳሌ
26 በረዶ በበጋ፣ ዝናብም በመከር እንደማያስፈልግ ሁሉ
ክብርም ለሞኝ ሰው አይገባውም።+
2 ወፍ ቱር የምትልበት፣ ወንጭፊትም የምትበርበት ምክንያት እንዳላት ሁሉ
እርግማንም ያለበቂ ምክንያት አይመጣም።*
4 ለሞኝ እንደ ሞኝነቱ አትመልስለት፤
አለዚያ አንተም የእሱ ቢጤ ትሆናለህ።*
5 ጥበበኛ የሆነ እንዳይመስለው
ለሞኝ እንደ ሞኝነቱ መልስለት።+
6 አንድን ጉዳይ ለሞኝ በአደራ የሚሰጥ
እግሩን ከሚያሽመደምድና ራሱን ከሚጎዳ* ሰው ተለይቶ አይታይም።
8 ለሞኝ ክብር መስጠት፣
በወንጭፍ ላይ ድንጋይ እንደ ማሰር ነው።+
9 በሞኞች አፍ የሚነገር ምሳሌ
በሰካራም እጅ እንዳለ እሾህ ነው።
10 ሞኝን ወይም አላፊ አግዳሚውን የሚቀጥር፣
በነሲብ ያገኘውን ሁሉ* እንደሚያቆስል ቀስተኛ ነው።
11 ውሻ ወደ ትፋቱ እንደሚመለስ፣
ሞኝ ሰውም ሞኝነቱን ይደጋግማል።+
12 ጥበበኛ ነኝ ብሎ የሚያስብ ሰው አይተህ ታውቃለህ?+
ከእሱ ይልቅ ሞኝ የተሻለ ተስፋ አለው።
13 ሰነፍ “በመንገድ ላይ ደቦል አንበሳ፣
በአደባባይም አንበሳ አለ!” ይላል።+
16 ሰነፍ ሰው በማስተዋል መልስ ከሚሰጡ ሰባት ሰዎች ይበልጥ
ጥበበኛ የሆነ ይመስለዋል።
18 የሚንበለበሉ ተወንጫፊ መሣሪያዎችን፣ ፍላጻዎችንና ሞትን* እንደሚወረውር እብድ፣
19 ባልንጀራውን አታሎ ሲያበቃ “ቀልዴን እኮ ነው!” የሚል ሰውም እንዲሁ ነው።+
20 እንጨት ከሌለ እሳት ይጠፋል፤
ስም አጥፊ ከሌለ ደግሞ ጭቅጭቅ ይበርዳል።+
21 ከሰል ፍምን፣ እንጨትም እሳትን እንደሚያቀጣጥል
ጨቅጫቃ ሰውም ጠብ ይጭራል።+
24 ሌሎችን የሚጠላ ሰው ጥላቻውን በከንፈሩ ይደብቃል፤
በውስጡ ግን ተንኮል ይቋጥራል።
25 አነጋገሩን ቢያሳምርም እንኳ አትመነው፤
በልቡ ውስጥ ሰባት አስጸያፊ ነገሮች አሉና።*
26 ጥላቻው በተንኮል ቢሸፈንም
ክፋቱ በጉባኤ መካከል ይገለጣል።
27 ጉድጓድ የሚቆፍር እሱ ራሱ እዚያ ውስጥ ይወድቃል፤
ድንጋይ የሚያንከባልልም ወደ እሱ ተመልሶ ይመጣበታል።+
28 ውሸታም ምላስ የጎዳቻቸውን ሰዎች ትጠላለች፤
የሚሸነግል አንደበትም ጥፋት ያስከትላል።+