ኢሳይያስ
27 በዚያን ቀን ይሖዋ፣ በፍጥነት እየተሳበ የሚሄደውን እባብ ሌዋታንን፣*
ደግሞም እየተጥመለመለ የሚጓዘውን እባብ ሌዋታንን
ትልቅ፣ ኃይለኛና ምሕረት የለሽ በሆነው ሰይፉ ይቀጣዋል፤+
በባሕር ውስጥ ያለውንም ግዙፍ ፍጥረት ይገድለዋል።
“የሚፈላ የወይን ጠጅ የሚመረትባት የወይን እርሻ!+
በየጊዜው ውኃ አጠጣታለሁ።+
ማንም ጉዳት እንዳያደርስባት
ሌት ተቀን እጠብቃታለሁ።+
በውጊያው ላይ ቁጥቋጦና አረም ይዞ የሚገጥመኝ ማን ነው?
ሁሉንም በአንድ ላይ እረግጣቸዋለሁ፤ በእሳትም አቃጥላቸዋለሁ።
5 አለዚያ ምሽጌን የሙጥኝ ይበል።
ከእኔ ጋር ሰላም ይፍጠር፤
አዎ፣ ከእኔ ጋር ሰላም ይፍጠር።”
7 እሱ አሁን በተመታበት ሁኔታ መመታቱ ተገቢ ነው?
ወይስ የተገደሉበት ሰዎች በተፈጁበት መንገድ መገደሉ አስፈላጊ ነው?
8 እሷን በምትልካት ጊዜ በአስደንጋጭ ጩኸት ትፋለማታለህ።
የምሥራቅ ነፋስ በሚነፍስበት ቀን በኃይለኛ አውሎ ነፋሱ ያስወግዳታል።+
10 የተመሸገችው ከተማ ትተዋለችና፤
የግጦሽ መሬቱም ወና ይሆናል፤ እንደ ምድረ በዳም የተተወ ይሆናል።+
በዚያ ጥጃ ይግጣል፤ ይተኛልም፤
ቅርንጫፎቿንም ይበላል።+
ይህ ሕዝብ ማስተዋል ይጎድለዋልና።+
በዚህም ምክንያት ፈጣሪያቸው ምንም ምሕረት አያደርግላቸውም፤
ሠሪያቸውም ምንም ዓይነት ሞገስ አያሳያቸውም።+
12 በዚያም ቀን የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ ሰው ዛፍ ላይ ያሉ ፍሬዎችን አርግፎ አንድ በአንድ እንደሚለቅም ሁሉ፣ ይሖዋም ከታላቁ ወንዝ* አንስቶ እስከ ግብፅ ደረቅ ወንዝ*+ ድረስ ባለው ቦታ ሁሉ የተበተናችሁትን ይሰበስባችኋል።+ 13 በዚያም ቀን ትልቅ ቀንደ መለከት ይነፋል፤+ በአሦር ምድር+ የጠፉትና በግብፅ ምድር+ የተበተኑት መጥተው በኢየሩሳሌም በሚገኘው ቅዱስ ተራራ ላይ ለይሖዋ ይሰግዳሉ።+