ኢሳይያስ
4 በዚያን ቀን ሰባት ሴቶች አንድን ወንድ ይዘው እንዲህ ይሉታል፦+
2 በዚያን ቀን፣ ይሖዋ እንዲያቆጠቁጥ ያደረገው ተክል ያማረና ክብር የተላበሰ ይሆናል፤ የምድሪቱም ፍሬ ከጥፋት ለተረፉት እስራኤላውያን የኩራት ምንጭና ውበት ይሆንላቸዋል።+ 3 በጽዮን የቀሩትና በኢየሩሳሌም የተረፉት ሁሉ ይኸውም በኢየሩሳሌም እንዲኖሩ የተመዘገቡት በጠቅላላ ቅዱሳን ተብለው ይጠራሉ።+
4 ይሖዋ በፍርድ መንፈስና በሚነድ* መንፈስ+ የጽዮንን ሴቶች ልጆች ቆሻሻ* አጥቦ ያስወግዳል፤+ የኢየሩሳሌምንም የደም ዕዳ ከመካከሏ አጥቦ ያነጻል፤ 5 ያን ጊዜ ይሖዋ በመላው የጽዮን ተራራ ላይና በመሰብሰቢያ ቦታዋ ላይ በቀን ደመናና ጭስ፣ በሌሊት ደግሞ የሚንበለበል የእሳት ብርሃን ይፈጥራል፤+ እንዲሁም ክብራማ በሆነው ቦታ ሁሉ ላይ መጠለያ ይኖራል። 6 ደግሞም በቀን ካለው ንዳድ ጥላ+ እንዲሁም ከውሽንፍርና ከዝናብ መጠጊያና መሸሸጊያ+ የሚሆን ዳስ ይኖራል።