ሰቆቃወ ኤርምያስ
א [አሌፍ]*
1 በሰዎች ተሞልታ የነበረችው ከተማ አሁን እንዴት ብቻዋን ቀረች!+
ከሌሎች ብሔራት ይበልጥ ብዙ ሕዝብ የነበረባት ከተማ እንዴት እንደ መበለት ሆነች!+
በአውራጃዎች መካከል ልዕልት የነበረችው ከተማ እንዴት ለባርነት ተዳረገች!+
ב [ቤት]
2 በሌሊት አምርራ ታለቅሳለች፤+ እንባዋም በጉንጮቿ ላይ ይወርዳል።
ከወዳጆቿ ሁሉ መካከል አንድም የሚያጽናናት የለም።+
ባልንጀሮቿ ሁሉ ከድተዋታል፤+ ጠላት ሆነውባታል።
ג [ጊሜል]
3 ይሁዳ ተጎሳቁላና ለአስከፊ ባርነት ተዳርጋ+ በግዞት ተወስዳለች።+
በብሔራት መካከል ትቀመጣለች፤+ ምንም ማረፊያ ስፍራ አታገኝም።
በተጨነቀች ጊዜ አሳዳጆቿ ሁሉ ያዟት።
ד [ዳሌት]
4 በዓል ለማክበር የሚመጣ ስለሌለ ወደ ጽዮን የሚወስዱት መንገዶች አዝነዋል።+
በሮቿ ሁሉ ወና ሆነዋል፤+ ካህናቷም ሲቃ ይዟቸዋል።
ደናግሏ* አዝነዋል፤ እሷም አስከፊ ሥቃይ ደርሶባታል።
ה [ሄ]
5 ባላጋራዎቿ አሁን ጌቶቿ* ሆነዋል፤ ጠላቶቿ ጭንቀት የለባቸውም።+
ከበደሏ ብዛት የተነሳ ይሖዋ ሐዘን አምጥቶባታልና።+
ልጆቿ በጠላት ፊት ተማርከው ተወስደዋል።+
ו [ዋው]
6 የጽዮን ሴት ልጅ፣ ግርማ ሞገሷ ሁሉ ተገፏል።+
መኳንንቷ መሰማሪያ ቦታ እንዳጡ አጋዘኖች ሆነዋል፤
በሚያሳድዳቸውም ፊት አቅም አጥተው ይጓዛሉ።
ז [ዛየን]
7 ኢየሩሳሌም በምትጎሳቆልበትና መኖሪያ በምታጣበት ጊዜ፣
በጥንት ዘመን የነበሯትን ውድ ነገሮች ሁሉ ታስታውሳለች።+
ח[ኼት]
8 ኢየሩሳሌም ከባድ ኃጢአት ፈጽማለች።+
አስጸያፊ ነገር የሆነችው ለዚህ ነው።
ያከብሯት የነበሩ ሁሉ አሁን ናቋት፤ እርቃኗን አይተዋልና።+
እሷ ራሷም ትቃትታለች፤+ በኀፍረትም ፊቷን ታዞራለች።
ט [ቴት]
9 ርኩሰቷ ቀሚሷ ላይ አለ።
ወደፊት የሚገጥማትን ቆም ብላ አላሰበችም።+
ውድቀቷ አስደንጋጭ ነበር፤ የሚያጽናናትም የለም።
ይሖዋ ሆይ፣ ጉስቁልናዬን ተመልከት፤ ጠላት ራሱን ከፍ ከፍ አድርጓልና።+
י [ዮድ]
10 ጠላት በውድ ሀብቶቿ ሁሉ ላይ እጁን አሳርፏል።+
ወደ አንተ ጉባኤ እንዳይገቡ ያዘዝካቸው ብሔራት
ወደ መቅደሷ ሲገቡ አይታለችና።+
כ [ካፍ]
11 ነዋሪዎቿ ሁሉ ሲቃ ይዟቸዋል፤ የሚበላ ነገር ይፈልጋሉ።+
ምግብ ለማግኘትና በሕይወት ለመቆየት* ብቻ ሲሉ ያሏቸውን ውድ ነገሮች ሰጥተዋል።
ይሖዋ ሆይ፣ እይ ደግሞም ተመልከት፤ እንደማትረባ ሴት ሆኛለሁና።*
ל [ላሜድ]
12 በዚህ መንገድ የምታልፉ ሁሉ፣ ይህ ለእናንተ ከምንም የማይቆጠር ነገር ነው?
እዩ፤ ደግሞም ተመልከቱ!
ይሖዋ በሚነድ ቁጣው ቀን እንድሠቃይ ያደረገበትን፣
በእኔ ላይ የደረሰውን ሥቃይ የመሰለ ሥቃይ አለ?+
מ [ሜም]
13 ከከፍታ ቦታ ወደ አጥንቶቼ እሳት ላከ፤+ በእያንዳንዳቸውም ላይ አየለባቸው።
ለእግሬ መረብ ዘረጋ፤ ወደ ኋላ እንድመለስ አስገደደኝ።
የተጣለች ሴት አድርጎኛል።
ቀኑን ሙሉ ታምሜአለሁ።
נ [ኑን]
14 በደሎቼ እንደ ቀንበር ታስረዋል፤ በእጁም ተገምደዋል።
አንገቴ ላይ ተደርገዋል፤ ጉልበቴም ተዳክሟል።
ይሖዋ መቋቋም ለማልችላቸው ሰዎች አሳልፎ ሰጥቶኛል።+
ס [ሳሜኽ]
15 ይሖዋ በውስጤ ያሉትን ኃያላን በሙሉ አስወገደ።+
ወጣቶቼን ለማድቀቅ በእኔ ላይ ጉባኤ ጠርቷል።+
ይሖዋ ድንግሊቱን የይሁዳን ልጅ በወይን መጭመቂያ ውስጥ ረግጧል።+
ע [አይን]
16 በእነዚህ ነገሮች የተነሳ አለቅሳለሁ፤+ ዓይኖቼ እንባ ያፈሳሉ።
ሊያጽናናኝ ወይም መንፈሴን* ሊያድስ የሚችል ሰው ከእኔ ርቋልና።
ወንዶች ልጆቼ ተጥለዋል፤ ጠላት አይሏልና።
פ [ፔ]
17 ጽዮን እጆቿን ዘረጋች፤+ የሚያጽናናትም የለም።
በያዕቆብ ዙሪያ ያሉት ሁሉ ጠላቶቹ እንዲሆኑ ይሖዋ ትእዛዝ አስተላልፏል።+
ኢየሩሳሌም ለእነሱ አስጸያፊ ነገር ሆናለች።+
צ [ጻዴ]
18 ይሖዋ ጻድቅ ነው፤+ ትእዛዙን ተላልፌአለሁና።*+
እናንተ ሰዎች ሁሉ፣ አዳምጡ፤ ሥቃዬንም ተመልከቱ።
ק [ኮፍ]
19 ወዳጆቼን ጠራኋቸው፤ እነሱ ግን ከዱኝ።+
ר [ረሽ]
20 ይሖዋ ሆይ፣ ተመልከት፤ በከባድ ጭንቀት ተውጫለሁና።
አንጀቴም ተላወሰ።
ልቤ በውስጤ እጅግ ተረብሿል፤ የለየለት ዓመፀኛ ሆኛለሁና።+
በውጭ ሰይፍ ይፈጃል፤+ በቤት ውስጥ ደግሞ ሞት አለ።
ש [ሺን]
21 ሰዎች ሲቃዬን ሰምተዋል፤ የሚያጽናናኝም የለም።
ጠላቶቼ ሁሉ ስለደረሰብኝ ጥፋት ሰምተዋል።
ይህን ጥፋት ስላመጣህ ደስ ተሰኝተዋል።+
አንተ ግን የተናገርከውን ቀን በእነሱ ላይ ታመጣለህ፤+ በዚያን ጊዜ እነሱ እንደ እኔ ይሆናሉ።+
ת [ታው]
22 ክፋታቸው ሁሉ በፊትህ ይቅረብ፤ በሠራኋቸው በደሎች ሁሉ የተነሳ
እኔን እንደቀጣኸኝ፣ እነሱንም ቅጣቸው።+
ለቅሶዬ በዝቷልና፤ ልቤም ታሟል።