-
ዕብራውያን 9:24-26አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
24 ክርስቶስ የገባው በሰው እጅ ወደተሠራውና የእውነተኛው ቅዱስ ስፍራ አምሳያ+ ወደሆነው ስፍራ አይደለምና፤+ ከዚህ ይልቅ አሁን ስለ እኛ በአምላክ ፊት ይታይ ዘንድ+ ወደ ሰማይ ገብቷል።+ 25 የገባው ግን ሊቀ ካህናቱ የራሱን ሳይሆን የእንስሳ ደም ይዞ በየዓመቱ ወደ ቅዱሱ ስፍራ ይገባ እንደነበረው ራሱን ብዙ ጊዜ መሥዋዕት አድርጎ ለማቅረብ አይደለም።+ 26 አለዚያማ ዓለም ከተመሠረተ* ጀምሮ ብዙ ጊዜ መከራ መቀበል ባስፈለገው ነበር። አሁን ግን ራሱን መሥዋዕት አድርጎ በማቅረብ ኃጢአትን ለማስወገድ በሥርዓቶቹ* መደምደሚያ ላይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ራሱን ገልጧል።+
-