ዘዳግም 1:32, 33 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 32 እናንተ ግን ይህ ሁሉ ተደርጎላችሁም በአምላካችሁ በይሖዋ ላይ እምነት አላሳደራችሁም፤+ 33 እሱ የምትሰፍሩበትን ቦታ ለመፈለግ ከፊት ከፊታችሁ ይሄድ ነበር። በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለባችሁ ለማሳየትም ሌሊት ሌሊት በእሳት፣ ቀን ቀን ደግሞ በደመና ይመራችሁ ነበር።+ ኢያሱ 3:3, 4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ሕዝቡን እንዲህ በማለት አዘዙ፦ “ሌዋውያን የሆኑት ካህናት+ የአምላካችሁን የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት ተሸክመው ስታዩ ከሰፈራችሁበት ቦታ ተነስታችሁ ታቦቱን ተከተሉት። 4 ሆኖም ወደ እሱ አትቅረቡ፤ በእናንተና በታቦቱ መካከል 2,000 ክንድ* ያህል ርቀት ይኑር፤ ከዚህ በፊት በዚህ አቅጣጫ ሄዳችሁ ስለማታውቁ በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለባችሁ በዚህ ትረዳላችሁ።”
32 እናንተ ግን ይህ ሁሉ ተደርጎላችሁም በአምላካችሁ በይሖዋ ላይ እምነት አላሳደራችሁም፤+ 33 እሱ የምትሰፍሩበትን ቦታ ለመፈለግ ከፊት ከፊታችሁ ይሄድ ነበር። በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለባችሁ ለማሳየትም ሌሊት ሌሊት በእሳት፣ ቀን ቀን ደግሞ በደመና ይመራችሁ ነበር።+
3 ሕዝቡን እንዲህ በማለት አዘዙ፦ “ሌዋውያን የሆኑት ካህናት+ የአምላካችሁን የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት ተሸክመው ስታዩ ከሰፈራችሁበት ቦታ ተነስታችሁ ታቦቱን ተከተሉት። 4 ሆኖም ወደ እሱ አትቅረቡ፤ በእናንተና በታቦቱ መካከል 2,000 ክንድ* ያህል ርቀት ይኑር፤ ከዚህ በፊት በዚህ አቅጣጫ ሄዳችሁ ስለማታውቁ በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለባችሁ በዚህ ትረዳላችሁ።”