2 ነገሥት 23:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ንጉሡ ዓምዱ አጠገብ ቆሞ በዚህ መጽሐፍ ላይ የሰፈሩትን የዚህን ቃል ኪዳን ቃላት በመፈጸም በሙሉ ልቡና በሙሉ ነፍሱ* ይሖዋን ለመከተል እንዲሁም ትእዛዛቱን፣ ማሳሰቢያዎቹንና ደንቦቹን ለመጠበቅ በይሖዋ ፊት ቃል ኪዳን ገባ።*+ ሕዝቡም ሁሉ በቃል ኪዳኑ ተስማማ።+ 2 ዜና መዋዕል 15:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 በተጨማሪም የአባቶቻቸውን አምላክ ይሖዋን በሙሉ ልባቸውና በሙሉ ነፍሳቸው* ለመፈለግ ቃል ኪዳን ገቡ።+ ዕዝራ 10:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 እንግዲህ ይሖዋም ሆነ ለአምላካችን ትእዛዝ አክብሮት ያላቸው* ሰዎች+ በሰጡት መመሪያ መሠረት ሚስቶቻችንን በሙሉና ከእነሱ የተወለዱትን ልጆች ለማሰናበት ከአምላካችን ጋር ቃል ኪዳን እንጋባ።+ ሕጉንም ተግባራዊ እናድርግ።
3 ንጉሡ ዓምዱ አጠገብ ቆሞ በዚህ መጽሐፍ ላይ የሰፈሩትን የዚህን ቃል ኪዳን ቃላት በመፈጸም በሙሉ ልቡና በሙሉ ነፍሱ* ይሖዋን ለመከተል እንዲሁም ትእዛዛቱን፣ ማሳሰቢያዎቹንና ደንቦቹን ለመጠበቅ በይሖዋ ፊት ቃል ኪዳን ገባ።*+ ሕዝቡም ሁሉ በቃል ኪዳኑ ተስማማ።+
3 እንግዲህ ይሖዋም ሆነ ለአምላካችን ትእዛዝ አክብሮት ያላቸው* ሰዎች+ በሰጡት መመሪያ መሠረት ሚስቶቻችንን በሙሉና ከእነሱ የተወለዱትን ልጆች ለማሰናበት ከአምላካችን ጋር ቃል ኪዳን እንጋባ።+ ሕጉንም ተግባራዊ እናድርግ።