ዘሌዋውያን 19:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 “‘በሕዝብህ መካከል እየዞርክ ስም አታጥፋ።+ በባልንጀራህ ሕይወት* ላይ አትነሳ።*+ እኔ ይሖዋ ነኝ። መዝሙር 101:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 የባልንጀራውን ስም በስውር የሚያጠፋን ሰው፣+ጸጥ አሰኘዋለሁ።* ትዕቢተኛ ዓይንና እብሪተኛ ልብ ያለውን ሰው፣አልታገሠውም። ምሳሌ 20:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 ስም የሚያጠፋ ሰው እየዞረ የሌሎችን ሚስጥር ይገልጣል፤+ማማት ከሚወድ ሰው* ጋር አትወዳጅ።