ዘፀአት 17:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 እኔም በዚያ በኮሬብ በሚገኘው ዓለት ላይ ፊትህ እቆማለሁ። አንተም ዓለቱን ትመታዋለህ፤ ውኃም ከውስጡ ይፈልቃል፤ ሕዝቡም ይጠጣሉ።”+ ሙሴም የእስራኤል ሽማግሌዎች እያዩ እንደተባለው አደረገ። ዘኁልቁ 20:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ሙሴም ይህን ካለ በኋላ እጁን አንስቶ ዓለቱን ሁለት ጊዜ በበትሩ መታው፤ ውኃውም ይንዶለዶል ጀመር፤ ማኅበረሰቡና ከብቶቻቸውም ጠጡ።+ ዘዳግም 8:14, 15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ልብህ እንዳይታበይና+ ከግብፅ ምድር ይኸውም ከባርነት ቤት ያወጣህን አምላክህን ይሖዋን እንዳያስረሳህ ተጠንቀቅ፤+ 15 መርዛማ እባቦችና ጊንጦች በሞሉበት እንዲሁም ውኃ የተጠማ ደረቅ ምድር ባለበት በዚያ ጭልጥ ያለና የሚያስፈራ ምድረ በዳ+ አቋርጠህ እንድታልፍ ያደረገህን አምላክህን እንዳያስረሳህ ተጠንቀቅ። እሱ ከጠንካራ ዓለት* ውኃ አፍልቆልሃል፤+ መዝሙር 107:35 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 35 በረሃውን ቄጠማ የሞላበት ኩሬ፣ደረቁንም ምድር የውኃ ምንጭ ያደርጋል።+
6 እኔም በዚያ በኮሬብ በሚገኘው ዓለት ላይ ፊትህ እቆማለሁ። አንተም ዓለቱን ትመታዋለህ፤ ውኃም ከውስጡ ይፈልቃል፤ ሕዝቡም ይጠጣሉ።”+ ሙሴም የእስራኤል ሽማግሌዎች እያዩ እንደተባለው አደረገ።
14 ልብህ እንዳይታበይና+ ከግብፅ ምድር ይኸውም ከባርነት ቤት ያወጣህን አምላክህን ይሖዋን እንዳያስረሳህ ተጠንቀቅ፤+ 15 መርዛማ እባቦችና ጊንጦች በሞሉበት እንዲሁም ውኃ የተጠማ ደረቅ ምድር ባለበት በዚያ ጭልጥ ያለና የሚያስፈራ ምድረ በዳ+ አቋርጠህ እንድታልፍ ያደረገህን አምላክህን እንዳያስረሳህ ተጠንቀቅ። እሱ ከጠንካራ ዓለት* ውኃ አፍልቆልሃል፤+