ዘፀአት 15:9, 10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ጠላትም ‘አሳድዳቸዋለሁ! አሳድጄ እደርስባቸዋለሁ! እስክጠግብም* ድረስ ምርኮን እከፋፈላለሁ! ሰይፌን እመዛለሁ! እጄም ታንበረክካቸዋለች!’ አለ።+ 10 አንተም እስትንፋስህን እፍ አልክ፤ ባሕሩም ከደናቸው፤+ እነሱም ኃያል በሆኑ ውኃዎች ውስጥ እንደ አረር ሰመጡ። ሉቃስ 12:18-20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 ከዚያም እንዲህ አለ፦ ‘እንዲህ አደርጋለሁ፦+ ያሉኝን ጎተራዎች አፈርስና ትላልቅ ጎተራዎች እሠራለሁ፤ በዚያም እህሌንና ንብረቴን ሁሉ አከማቻለሁ፤ 19 ነፍሴንም* “ነፍሴ* ሆይ፣ ለብዙ ዘመን የሚበቃ የተከማቸ ሀብት አለሽ፤ እንግዲህ ዘና በይ፣ ብዪ፣ ጠጪ፣ ደስም ይበልሽ” እላታለሁ።’ 20 አምላክ ግን ‘አንተ ማስተዋል የጎደለህ፣ በዚህች ሌሊት ሕይወትህን* ይፈልጓታል። ታዲያ ያከማቸኸው ነገር ለማን ይሆናል?’ አለው።+
9 ጠላትም ‘አሳድዳቸዋለሁ! አሳድጄ እደርስባቸዋለሁ! እስክጠግብም* ድረስ ምርኮን እከፋፈላለሁ! ሰይፌን እመዛለሁ! እጄም ታንበረክካቸዋለች!’ አለ።+ 10 አንተም እስትንፋስህን እፍ አልክ፤ ባሕሩም ከደናቸው፤+ እነሱም ኃያል በሆኑ ውኃዎች ውስጥ እንደ አረር ሰመጡ።
18 ከዚያም እንዲህ አለ፦ ‘እንዲህ አደርጋለሁ፦+ ያሉኝን ጎተራዎች አፈርስና ትላልቅ ጎተራዎች እሠራለሁ፤ በዚያም እህሌንና ንብረቴን ሁሉ አከማቻለሁ፤ 19 ነፍሴንም* “ነፍሴ* ሆይ፣ ለብዙ ዘመን የሚበቃ የተከማቸ ሀብት አለሽ፤ እንግዲህ ዘና በይ፣ ብዪ፣ ጠጪ፣ ደስም ይበልሽ” እላታለሁ።’ 20 አምላክ ግን ‘አንተ ማስተዋል የጎደለህ፣ በዚህች ሌሊት ሕይወትህን* ይፈልጓታል። ታዲያ ያከማቸኸው ነገር ለማን ይሆናል?’ አለው።+