ኢሳይያስ 2:2, 3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 በዘመኑ መጨረሻ*የይሖዋ ቤት ተራራከተራሮች አናት በላይ ጸንቶ ይቆማል፤+ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ብሔራትም ሁሉ ወደዚያ ይጎርፋሉ።+ 3 ብዙ ሕዝቦችም ሄደው እንዲህ ይላሉ፦ “ኑ፤ ወደ ይሖዋ ተራራ፣ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ።+ እሱ ስለ መንገዶቹ ያስተምረናል፤በጎዳናዎቹም እንሄዳለን።”+ ሕግ* ከጽዮን፣የይሖዋም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።+ ኢሳይያስ 56:6, 7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 እሱን ለማገልገል፣ የይሖዋን ስም ለመውደድናየእሱ አገልጋዮች ለመሆንከይሖዋ ጋር የሚቆራኙትን የባዕድ አገር ሰዎች፣+ሰንበትን የሚጠብቁትንና የማያረክሱትን፣ቃል ኪዳኔንም አጥብቀው የሚይዙትን ሁሉ፣ 7 ቅዱስ ወደሆነው ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፤+በጸሎት ቤቴም ውስጥ እጅግ እንዲደሰቱ አደርጋቸዋለሁ። የሚያቀርቧቸውም ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎችና መሥዋዕቶች በመሠዊያዬ ላይ ተቀባይነት ያገኛሉ። ቤቴም ለሕዝቦች ሁሉ የጸሎት ቤት ተብሎ ይጠራልና።”+ ኢሳይያስ 60:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ብሔራት ወደ ብርሃንሽ፣+ነገሥታትም+ አንጸባራቂ ወደሆነው ውበትሽ* ይመጣሉ።+ ሚክያስ 4:1, 2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 በዘመኑ መጨረሻ*የይሖዋ ቤት ተራራ+ከተራሮች አናት በላይ ጸንቶ ይቆማል፤ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ሕዝቦችም ወደዚያ ይጎርፋሉ።+ 2 ብዙ ብሔራትም ሄደው እንዲህ ይላሉ፦ “ኑ፤ ወደ ይሖዋ ተራራናወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ።+ እሱ ስለ መንገዶቹ ያስተምረናል፤በጎዳናዎቹም እንሄዳለን።” ሕግ* ከጽዮን፣የይሖዋም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና። ዘካርያስ 2:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 “በዚያን ቀን ብዙ ብሔራት ከይሖዋ ጋር ይተባበራሉ፤+ እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም በመካከልሽ እኖራለሁ።” ደግሞም እኔን ወደ አንቺ የላከኝ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንደሆነ ታውቂያለሽ። ዘካርያስ 8:22, 23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 ደግሞም ብዙ ሕዝቦችና ኃያላን ብሔራት የሠራዊት ጌታ ይሖዋን ለመፈለግና ይሖዋ ሞገሱን እንዲያሳያቸው ለመለመን ወደ ኢየሩሳሌም ይመጣሉ።’+ 23 “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በዚያን ጊዜ ከብሔራት ቋንቋዎች ሁሉ የተውጣጡ+ አሥር ሰዎች የአንድን አይሁዳዊ ልብስ* አጥብቀው በመያዝ “አምላክ ከእናንተ ጋር መሆኑን ስለሰማን ከእናንተ ጋር እንሄዳለን”+ ይላሉ።’”+
2 በዘመኑ መጨረሻ*የይሖዋ ቤት ተራራከተራሮች አናት በላይ ጸንቶ ይቆማል፤+ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ብሔራትም ሁሉ ወደዚያ ይጎርፋሉ።+ 3 ብዙ ሕዝቦችም ሄደው እንዲህ ይላሉ፦ “ኑ፤ ወደ ይሖዋ ተራራ፣ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ።+ እሱ ስለ መንገዶቹ ያስተምረናል፤በጎዳናዎቹም እንሄዳለን።”+ ሕግ* ከጽዮን፣የይሖዋም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።+
6 እሱን ለማገልገል፣ የይሖዋን ስም ለመውደድናየእሱ አገልጋዮች ለመሆንከይሖዋ ጋር የሚቆራኙትን የባዕድ አገር ሰዎች፣+ሰንበትን የሚጠብቁትንና የማያረክሱትን፣ቃል ኪዳኔንም አጥብቀው የሚይዙትን ሁሉ፣ 7 ቅዱስ ወደሆነው ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፤+በጸሎት ቤቴም ውስጥ እጅግ እንዲደሰቱ አደርጋቸዋለሁ። የሚያቀርቧቸውም ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎችና መሥዋዕቶች በመሠዊያዬ ላይ ተቀባይነት ያገኛሉ። ቤቴም ለሕዝቦች ሁሉ የጸሎት ቤት ተብሎ ይጠራልና።”+
4 በዘመኑ መጨረሻ*የይሖዋ ቤት ተራራ+ከተራሮች አናት በላይ ጸንቶ ይቆማል፤ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ሕዝቦችም ወደዚያ ይጎርፋሉ።+ 2 ብዙ ብሔራትም ሄደው እንዲህ ይላሉ፦ “ኑ፤ ወደ ይሖዋ ተራራናወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ።+ እሱ ስለ መንገዶቹ ያስተምረናል፤በጎዳናዎቹም እንሄዳለን።” ሕግ* ከጽዮን፣የይሖዋም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።
11 “በዚያን ቀን ብዙ ብሔራት ከይሖዋ ጋር ይተባበራሉ፤+ እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም በመካከልሽ እኖራለሁ።” ደግሞም እኔን ወደ አንቺ የላከኝ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንደሆነ ታውቂያለሽ።
22 ደግሞም ብዙ ሕዝቦችና ኃያላን ብሔራት የሠራዊት ጌታ ይሖዋን ለመፈለግና ይሖዋ ሞገሱን እንዲያሳያቸው ለመለመን ወደ ኢየሩሳሌም ይመጣሉ።’+ 23 “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በዚያን ጊዜ ከብሔራት ቋንቋዎች ሁሉ የተውጣጡ+ አሥር ሰዎች የአንድን አይሁዳዊ ልብስ* አጥብቀው በመያዝ “አምላክ ከእናንተ ጋር መሆኑን ስለሰማን ከእናንተ ጋር እንሄዳለን”+ ይላሉ።’”+