-
ዘኁልቁ 15:20አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
20 ከተፈጨው የእህላችሁ በኩር+ ላይ የቀለበት ቅርጽ ያለው ዳቦ በማዘጋጀት መዋጮ ማድረግ ይኖርባችኋል። ይህን ማዋጣት የሚኖርባችሁ ከአውድማ ላይ የሚገኘውን መዋጮ በምታዋጡበት መንገድ ነው።
-
-
ነህምያ 10:35-37አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
35 እንዲሁም መሬታችን የሚያፈራውን መጀመሪያ የደረሰውን ፍሬና ማንኛውም ዓይነት የፍራፍሬ ዛፍ የሚያፈራውን መጀመሪያ የደረሰውን ፍሬ ሁሉ በየዓመቱ ወደ ይሖዋ ቤት እናመጣለን፤+ 36 በተጨማሪም በሕጉ ላይ በተጻፈው መሠረት ከወንዶች ልጆቻችንና ከእንስሶቻችን በኩሩን+ እንዲሁም ከከብቶቻችንና ከመንጎቻችን በኩሩን እናመጣለን። ወደ አምላካችን ቤት ይኸውም በአምላካችን ቤት ወደሚያገለግሉት ካህናት እናመጣለን።+ 37 ከዚህም በተጨማሪ የተፈጨውን የእህላችንን በኩር፣+ መዋጮዎቻችንን፣ ማንኛውም ዛፍ የሚያፈራውን ፍሬ፣+ አዲስ የወይን ጠጅና ዘይት+ ወደ አምላካችን ቤት ግምጃ ቤቶች*+ ወደ ካህናቱ እናመጣለን፤ እንዲሁም ከእርሻ ከተሞቻችን ሁሉ አንድ አሥረኛውን* የሚቀበሉት ሌዋውያኑ ስለሆኑ የመሬታችንን አንድ አሥረኛ ለሌዋውያኑ እናመጣለን።+
-