-
ማርቆስ 10:2-12አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
2 ፈሪሳውያንም ቀርበው እሱን ለመፈተን በማሰብ አንድ ሰው ሚስቱን እንዲፈታ ሕግ ይፈቅድለት እንደሆነ ጠየቁት።+ 3 እሱም መልሶ “ሙሴ ምን ብሎ ነው ያዘዛችሁ?” አላቸው። 4 እነሱም “ሙሴ የፍቺ የምሥክር ወረቀት ጽፎ እንዲፈታት ፈቅዷል” አሉት።+ 5 ኢየሱስ ግን እንዲህ አላቸው፦ “ሙሴ ይህን ትእዛዝ የጻፈላችሁ ልባችሁ ደንዳና+ መሆኑን አይቶ ነው።+ 6 ይሁን እንጂ በፍጥረት መጀመሪያ ‘አምላክ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።+ 7 ከዚህ የተነሳ ሰው ከአባቱና ከእናቱ ይለያል፤+ 8 ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ’፤+ በመሆኑም ከዚህ በኋላ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ሁለት አይደሉም። 9 ስለዚህ አምላክ ያጣመረውን* ማንም ሰው አይለያየው።”+ 10 እንደገና ወደ ቤት በገቡ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ስለዚህ ጉዳይ ይጠይቁት ጀመር። 11 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “ሚስቱን ፈቶ ሌላ የሚያገባ ሁሉ በማመንዘር+ ሚስቱን ይበድላል፤ 12 አንዲት ሴትም ብትሆን ባሏን ፈታ ሌላ ብታገባ ታመነዝራለች።”+
-