1 ጢሞቴዎስ 6:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 በተጨማሪም መልካም ነገር እንዲያደርጉ፣ በመልካም ሥራዎች ባለጸጋ እንዲሆኑ እንዲሁም ለጋሶችና ለሌሎች ለማካፈል ዝግጁ እንዲሆኑ ምከራቸው፤+ ያዕቆብ 2:15, 16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 አንድ ወንድም ወይም አንዲት እህት የሚለብሱት ቢያጡና* ለዕለት የሚያስፈልጋቸውን በቂ ምግብ ባያገኙ 16 ሆኖም ከመካከላችሁ አንዱ “በሰላም ሂዱ፤ ይሙቃችሁ፤ ጥገቡም” ቢላቸው ለሰውነታቸው የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች ግን ባይሰጣቸው ምን ይጠቅማቸዋል?+ 1 ዮሐንስ 3:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ይሁን እንጂ የዚህ ዓለም ቁሳዊ ንብረት ያለው ሰው ወንድሙ ሲቸገር ተመልክቶ ሳይራራለት ቢቀር ‘የአምላክ ፍቅር በእሱ ውስጥ አለ’ እንዴት ሊባል ይችላል?+
15 አንድ ወንድም ወይም አንዲት እህት የሚለብሱት ቢያጡና* ለዕለት የሚያስፈልጋቸውን በቂ ምግብ ባያገኙ 16 ሆኖም ከመካከላችሁ አንዱ “በሰላም ሂዱ፤ ይሙቃችሁ፤ ጥገቡም” ቢላቸው ለሰውነታቸው የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች ግን ባይሰጣቸው ምን ይጠቅማቸዋል?+