ዘዳግም 15:7, 8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 “ከወንድሞችህ መካከል አንዱ አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ከሚገኙት ከተሞች በአንዱ ውስጥ ድሃ ቢሆን በድሃው ወንድምህ ላይ ልብህ አይጨክንበት ወይም እጅህን አትጠፍበት።+ 8 ከዚህ ይልቅ በልግስና እጅህን ዘርጋለት፤+ በተቻለ መጠን፣ የሚያስፈልገውን ወይም የጎደለውን ማንኛውንም ነገር አበድረው።* ማቴዎስ 25:35, 36 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 35 ምክንያቱም ተርቤ አብልታችሁኛል፤ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛል። እንግዳ ሆኜ አስተናግዳችሁኛል፤+ 36 ታርዤ* አልብሳችሁኛል።+ ታምሜ አስታማችሁኛል። ታስሬ ጠይቃችሁኛል።’+ ሉቃስ 3:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 እሱም መልሶ “ሁለት ልብስ* ያለው አንዱን ምንም ለሌለው ይስጥ፤ ምግብ ያለውም እንዲሁ ያድርግ” አላቸው።+ ሮም 12:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ለቅዱሳን እንደየችግራቸው ያላችሁን አካፍሉ።+ የእንግዳ ተቀባይነትን ባሕል አዳብሩ።+ 1 ጢሞቴዎስ 5:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ሆኖም አንዲት መበለት ልጆች ወይም የልጅ ልጆች ካሏት እነዚህ ልጆች በመጀመሪያ በራሳቸው ቤተሰብ+ ውስጥ ለአምላክ የማደርን ባሕርይ ማንጸባረቅን እንዲሁም ለወላጆቻቸውና ለአያቶቻቸው የሚገባቸውን ብድራት መክፈልን ይማሩ፤+ ይህ በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ነገር ነውና።+ ያዕቆብ 1:27 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 በአምላካችንና በአባታችን ዓይን ንጹሕና ያልረከሰ አምልኮ* ‘ወላጅ አልባ የሆኑ ልጆችንና+ መበለቶችን+ በመከራቸው መርዳት+ እንዲሁም ከዓለም እድፍ ራስን መጠበቅ’ ነው።+ 1 ዮሐንስ 3:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ይሁን እንጂ የዚህ ዓለም ቁሳዊ ንብረት ያለው ሰው ወንድሙ ሲቸገር ተመልክቶ ሳይራራለት ቢቀር ‘የአምላክ ፍቅር በእሱ ውስጥ አለ’ እንዴት ሊባል ይችላል?+
7 “ከወንድሞችህ መካከል አንዱ አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ከሚገኙት ከተሞች በአንዱ ውስጥ ድሃ ቢሆን በድሃው ወንድምህ ላይ ልብህ አይጨክንበት ወይም እጅህን አትጠፍበት።+ 8 ከዚህ ይልቅ በልግስና እጅህን ዘርጋለት፤+ በተቻለ መጠን፣ የሚያስፈልገውን ወይም የጎደለውን ማንኛውንም ነገር አበድረው።*
35 ምክንያቱም ተርቤ አብልታችሁኛል፤ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛል። እንግዳ ሆኜ አስተናግዳችሁኛል፤+ 36 ታርዤ* አልብሳችሁኛል።+ ታምሜ አስታማችሁኛል። ታስሬ ጠይቃችሁኛል።’+
4 ሆኖም አንዲት መበለት ልጆች ወይም የልጅ ልጆች ካሏት እነዚህ ልጆች በመጀመሪያ በራሳቸው ቤተሰብ+ ውስጥ ለአምላክ የማደርን ባሕርይ ማንጸባረቅን እንዲሁም ለወላጆቻቸውና ለአያቶቻቸው የሚገባቸውን ብድራት መክፈልን ይማሩ፤+ ይህ በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ነገር ነውና።+
27 በአምላካችንና በአባታችን ዓይን ንጹሕና ያልረከሰ አምልኮ* ‘ወላጅ አልባ የሆኑ ልጆችንና+ መበለቶችን+ በመከራቸው መርዳት+ እንዲሁም ከዓለም እድፍ ራስን መጠበቅ’ ነው።+