ዘሌዋውያን 19:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 “‘የሕዝብህን ልጆች አትበቀል፤+ በእነሱም ላይ ቂም አትያዝ፤ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ።+ እኔ ይሖዋ ነኝ። ማቴዎስ 19:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 አባትህንና እናትህን አክብር+ እንዲሁም ባልንጀራህን* እንደ ራስህ ውደድ።”+ ሮም 13:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ምክንያቱም “አታመንዝር፣+ አትግደል፣+ አትስረቅ፣+ አትጎምጅ”+ የሚሉት ሕጎችና ሌሎች ትእዛዛት በሙሉ “ባልንጀራህን* እንደ ራስህ ውደድ”+ በሚለው በዚህ ቃል ተጠቃለዋል። ገላትያ 5:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 መላው ሕግ “ባልንጀራህን* እንደ ራስህ ውደድ” በሚለው አንድ ትእዛዝ ተፈጽሟልና።*+ ያዕቆብ 2:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 እንግዲያው በቅዱስ መጽሐፉ መሠረት “ባልንጀራህን* እንደ ራስህ ውደድ”+ የሚለውን ንጉሣዊ ሕግ ተግባራዊ የምታደርጉ ከሆነ መልካም እያደረጋችሁ ነው።
9 ምክንያቱም “አታመንዝር፣+ አትግደል፣+ አትስረቅ፣+ አትጎምጅ”+ የሚሉት ሕጎችና ሌሎች ትእዛዛት በሙሉ “ባልንጀራህን* እንደ ራስህ ውደድ”+ በሚለው በዚህ ቃል ተጠቃለዋል።