-
ማቴዎስ 19:16-22አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
16 ከዚያም አንድ ወጣት ወደ እሱ መጥቶ “መምህር፣ የዘላለም ሕይወት ለማግኘት ምን ጥሩ ነገር ማድረግ ይኖርብኛል?” አለው።+ 17 እሱም “ስለ ጥሩ ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? ጥሩ የሆነው አምላክ ብቻ ነው።+ ሆኖም ሕይወት ማግኘት የምትፈልግ ከሆነ ዘወትር ትእዛዛቱን ጠብቅ” አለው።+ 18 እሱም “የትኞቹን?” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “አትግደል፣+ አታመንዝር፣+ አትስረቅ፣+ በሐሰት አትመሥክር፣+ 19 አባትህንና እናትህን አክብር+ እንዲሁም ባልንጀራህን* እንደ ራስህ ውደድ።”+ 20 ወጣቱም “እነዚህን ሁሉ ስጠብቅ ኖሬአለሁ፤ ታዲያ አሁን የሚጎድለኝ ነገር ምንድን ነው?” አለው። 21 ኢየሱስም “ፍጹም* መሆን ከፈለግክ ሂድና ንብረትህን ሸጠህ ገንዘቡን ለድሆች ስጥ፤ በሰማይም ውድ ሀብት ታገኛለህ፤+ ደግሞም መጥተህ ተከታዬ ሁን” አለው።+ 22 ወጣቱም ይህን ሲሰማ ብዙ ንብረት ስለነበረው እያዘነ ሄደ።+
-
-
ማርቆስ 10:17-22አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
17 ከዚያ ወጥቶ በመሄድ ላይ ሳለ አንድ ሰው እየሮጠ መጣ፤ በፊቱም በጉልበቱ ተንበርክኮ “ጥሩ መምህር ሆይ፣ የዘላለም ሕይወት ለመውረስ ምን ማድረግ ይኖርብኛል?” ሲል ጠየቀው።+ 18 ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “ለምን ጥሩ ብለህ ትጠራኛለህ? ከአንዱ ከአምላክ በቀር ጥሩ የለም።+ 19 ‘አትግደል፣+ አታመንዝር፣+ አትስረቅ፣+ በሐሰት አትመሥክር፣+ አታታል፣+ አባትህንና እናትህን አክብር’+ የሚሉትን ትእዛዛት ታውቃለህ።” 20 ሰውየውም “መምህር፣ እነዚህን ሁሉ ከልጅነቴ ጀምሮ ስጠብቅ ኖሬአለሁ” አለው። 21 ኢየሱስም ተመለከተውና ወደደው፤ ከዚያም “አንድ ነገር ይጎድልሃል፤ ሂድና ያለህን ነገር ሁሉ ሸጠህ ገንዘቡን ለድሆች ስጥ፤ በሰማይም ውድ ሀብት ታገኛለህ፤ ደግሞም መጥተህ ተከታዬ ሁን” አለው።+ 22 ሰውየው ግን ይህን ሲሰማ አዘነ፤ ብዙ ንብረት ስለነበረውም እያዘነ ሄደ።+
-