ምሳሌ 10:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 የጻድቅ መታሰቢያ* በረከት ያስገኛል፤+የክፉዎች ስም ግን ይጠፋል።*+ ዕብራውያን 10:26, 27 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 የእውነትን ትክክለኛ እውቀት ካገኘን በኋላ ሆን ብለን በኃጢአት ጎዳና ብንመላለስ+ ለኃጢአታችን የሚቀርብ ሌላ መሥዋዕት አይኖርም፤+ 27 ከዚህ ይልቅ አስፈሪ ፍርድ ይጠብቀናል፤ አምላክን የሚቃወሙትን የሚበላ የሚነድ ቁጣም ይኖራል።+ ራእይ 2:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 መንፈስ ለጉባኤዎቹ የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ፦+ ድል የሚነሳ+ በሁለተኛው ሞት+ ከቶ አይጎዳም።’ ራእይ 20:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 በመጀመሪያው ትንሣኤ ተካፋይ የሆኑ ሁሉ ደስተኞችና ቅዱሳን ናቸው፤+ ሁለተኛው ሞት+ በእነዚህ ላይ ሥልጣን የለውም፤+ ከዚህ ይልቅ የአምላክና የክርስቶስ ካህናት ይሆናሉ፤+ ከእሱም ጋር ለ1,000 ዓመት ይነግሣሉ።+
26 የእውነትን ትክክለኛ እውቀት ካገኘን በኋላ ሆን ብለን በኃጢአት ጎዳና ብንመላለስ+ ለኃጢአታችን የሚቀርብ ሌላ መሥዋዕት አይኖርም፤+ 27 ከዚህ ይልቅ አስፈሪ ፍርድ ይጠብቀናል፤ አምላክን የሚቃወሙትን የሚበላ የሚነድ ቁጣም ይኖራል።+
6 በመጀመሪያው ትንሣኤ ተካፋይ የሆኑ ሁሉ ደስተኞችና ቅዱሳን ናቸው፤+ ሁለተኛው ሞት+ በእነዚህ ላይ ሥልጣን የለውም፤+ ከዚህ ይልቅ የአምላክና የክርስቶስ ካህናት ይሆናሉ፤+ ከእሱም ጋር ለ1,000 ዓመት ይነግሣሉ።+