መዝሙር
78 ሕዝቤ ሆይ፣ ሕጌን* አዳምጥ፤
ከአፌ ወደሚወጣው ቃል ጆሮህን አዘንብል።
2 አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ።
በጥንት ዘመን የተነገሩትን እንቆቅልሾች አቀርባለሁ።+
3 የሰማናቸውንና ያወቅናቸውን ነገሮች፣
አባቶቻችን ለእኛ የተረኩልንን፣+
4 ከልጆቻቸው አንደብቀውም፤
ይሖዋ ያከናወናቸውን የሚያስመሰግኑ ሥራዎችና ብርታቱን፣+
ደግሞም የሠራቸውን አስደናቂ ነገሮች+
ለመጪው ትውልድ እንተርካለን።+
5 እሱ ለያዕቆብ ማሳሰቢያ ሰጠ፤
በእስራኤልም ሕግ ደነገገ፤
እነዚህን ነገሮች ለልጆቻቸው እንዲያሳውቁ
አባቶቻችንን አዘዛቸው፤+
6 ይህም ቀጣዩ ትውልድ፣
ገና የሚወለዱት ልጆች እነዚህን ነገሮች እንዲያውቁ ነው።+
እነሱም በተራቸው ለልጆቻቸው ይተርካሉ።+
7 በዚህ ጊዜ እነሱ ትምክህታቸውን በአምላክ ላይ ይጥላሉ።
9 ኤፍሬማውያን ቀስት የታጠቁ ነበሩ፤
ይሁንና በጦርነት ቀን ወደ ኋላ አፈገፈጉ።
11 በተጨማሪም ያደረጋቸውን ነገሮች፣
ያሳያቸውን ድንቅ ሥራዎች ረሱ።+
14 ቀን በደመና፣ ሌሊቱን ሙሉ ደግሞ
በእሳት ብርሃን መራቸው።+
15 በምድረ በዳ ዓለቶችን ሰነጠቀ፤
ከጥልቅ ውኃ የሚጠጡ ያህል እስኪረኩ ድረስ አጠጣቸው።+
16 ከቋጥኝ ውስጥ ወራጅ ውኃ አወጣ፤
ውኃዎችም እንደ ወንዝ እንዲፈስሱ አደረገ።+
19 “አምላክ በምድረ በዳ ማዕድ ማዘጋጀት ይችላል?” በማለት
በአምላክ ላይ አጉረመረሙ።+
20 እነሆ፣ ውኃ እንዲፈስና ጅረቶች እንዲንዶለዶሉ
ዓለትን መታ።+
ይሁንና “ዳቦስ ሊሰጠን ይችላል?
ወይስ ለሕዝቡ ሥጋ ሊያቀርብ ይችላል?” አሉ።+
21 ይሖዋ በሰማቸው ጊዜ እጅግ ተቆጣ፤+
በያዕቆብ ላይ እሳት+ ተቀጣጠለ፤
በእስራኤልም ላይ ቁጣው ነደደ፤+
22 ምክንያቱም በአምላክ ላይ እምነት አልጣሉም፤+
እነሱን የማዳን ችሎታ እንዳለው አላመኑም።
23 ስለዚህ በላይ ያሉትን በደመና የተሸፈኑ ሰማያት አዘዘ፤
የሰማይንም በሮች ከፈተ።
26 የምሥራቁን ነፋስ በሰማይ አስነሳ፤
በኃይሉም የደቡብ ነፋስ እንዲነፍስ አደረገ።+
27 ሥጋንም እንደ አፈር፣
ወፎችንም በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ አዘነበላቸው።
28 በሰፈሩ መካከል፣
በድንኳኖቹም ሁሉ ዙሪያ እንዲወድቁ አደረገ።
29 እነሱም በሉ፤ ከልክ በላይም ጠገቡ፤
የተመኙትን ነገር ሰጣቸው።+
ኃያላን ሰዎቻቸውን ገደለ፤+
የእስራኤልን ወጣቶች ጣለ።
33 ስለዚህ ዘመናቸው እንደ እስትንፋስ እንዲያበቃ፣+
ዕድሜያቸውም በድንገተኛ ሽብር እንዲያከትም አደረገ።
36 እነሱ ግን በአፋቸው ሊያታልሉት ሞከሩ፤
በምላሳቸውም ዋሹት።
ቁጣውን ሁሉ ከመቀስቀስ ይልቅ
ብዙ ጊዜ ስሜቱን ይገታ ነበር።+
42 እነሱን ከጠላት የታደገበትን* ቀን፣
43 በግብፅ አስደናቂ ምልክቶችን፣
በጾዓን ምድርም ተአምራቱን እንዴት እንዳሳየ አላሰቡም፤+
44 እንዲሁም ከጅረቶቻቸው መጠጣት እንዳይችሉ
የአባይን የመስኖ ቦዮች እንዴት ወደ ደም እንደለወጠ ዘነጉ።+
46 ሰብላቸውን ለማይጠግብ አንበጣ፣
የድካማቸውን ፍሬ ለአንበጣ መንጋ ሰጠ።+
47 የወይን ተክላቸውን በበረዶ፣
የሾላ ዛፎቻቸውንም በበረዶ ድንጋይ አጠፋ።+
49 የሚነድ ቁጣውን፣
ንዴቱን፣ መዓቱንና መቅሰፍቱን
እንዲሁም ጥፋት የሚያመጡ የመላእክት ሠራዊትን ላከባቸው።
50 ለቁጣው መንገድ ጠረገ።
ከሞት አላተረፋቸውም፤*
ለቸነፈርም አሳልፎ ሰጣቸው።
51 በመጨረሻም የግብፅን በኩሮች በሙሉ፣
በካም ድንኳኖች ውስጥ ከሚገኙትም መካከል የፍሬያቸው መጀመሪያ የሆኑትን መታ።+
52 ከዚያም ሕዝቡን እንደ በጎች እንዲወጡ አደረገ፤
በምድረ በዳም እንደ መንጋ መራቸው።+
54 ደግሞም ቅዱስ ወደሆነው ምድሩ፣
ቀኝ እጁ የራሱ ወዳደረገው ወደዚህ ተራራማ ክልል አመጣቸው።+
57 በተጨማሪም ጀርባቸውን ሰጡ፤ እንደ አባቶቻቸውም ከሃዲዎች ሆኑ።+
ጅማቱ እንደረገበ ደጋን እምነት የማይጣልባቸው ነበሩ።+
59 አምላክ ሰምቶ በጣም ተቆጣ፤+
በመሆኑም እስራኤልን እርግፍ አድርጎ ተወው።
60 በመጨረሻም በሴሎ የሚገኘውን የማደሪያ ድንኳን፣
በሰው ልጆች መካከል ይኖርበት የነበረውን ድንኳን ተወው።+
61 የብርታቱ ምልክት ተማርኮ እንዲወሰድ ፈቀደ፤
ግርማ ሞገሱን በጠላት እጅ አሳልፎ ሰጠ።+
62 ሕዝቡን ለሰይፍ አሳልፎ ሰጠ፤+
በርስቱም ላይ እጅግ ተቆጣ።
63 ወጣቶቹን እሳት በላቸው፤
ለድንግሎቹም የሠርግ ዘፈን አልተዘፈነላቸውም።*
65 ከዚያም ይሖዋ፣ የወይን ጠጅ ስካሩ እንደለቀቀው ኃያል ሰው
ከእንቅልፍ እንደነቃ ሆኖ ተነሳ።+
66 ጠላቶቹንም አሳዶ ወደ ኋላ መለሳቸው፤+
ለዘለቄታው ውርደት አከናነባቸው።
67 የዮሴፍን ድንኳን ናቀ፤
የኤፍሬምን ነገድ አልመረጠም።