መዝሙር
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በጊቲት።* የአሳፍ+ መዝሙር።
81 ብርታታችን ለሆነው አምላክ+ እልል በሉ።
ለያዕቆብ አምላክ በድል አድራጊነት ስሜት ጩኹ።
2 ሙዚቃውን መጫወት ጀምሩ፤ አታሞም ምቱ፤
ደስ የሚያሰኘውን በገና ከባለ አውታር መሣሪያ ጋር ተጫወቱ።
4 ይህ ለእስራኤል የተሰጠ ድንጋጌ፣
የያዕቆብም አምላክ ያስተላለፈው ውሳኔ ነውና።+
እኔም የማላውቀውን ድምፅ* ሰማሁ፦
6 “ሸክሙን ከትከሻው ላይ አነሳሁለት፤+
እጆቹ ቅርጫት ከመያዝ አረፉ።
የመሪባ* ውኃዎች ባሉበት ስፍራ ፈተንኩህ።+ (ሴላ)
8 ሕዝቤ ሆይ፣ ስማኝ፤ እኔም እመሠክርብሃለሁ።
እስራኤል ሆይ፣ ምነው ብታዳምጠኝ!+
9 በመካከልህ እንግዳ አምላክ አይኖርም፤
ለባዕድ አምላክም አትሰግድም።+
10 ከግብፅ ምድር ያወጣሁህ፣
እኔ ይሖዋ አምላክህ ነኝ።+
አፍህን በሰፊው ክፈት፤ እኔም በምግብ እሞላዋለሁ።+
11 ሕዝቤ ግን ድምፄን አልሰማም፤
እስራኤል ለእኔ አይገዛም።+
14 ጠላቶቻቸውን ወዲያውኑ ባንበረከክኋቸው፣
እጄን በባላጋራዎቻቸው ላይ በሰነዘርኩ ነበር።+
15 ይሖዋን የሚጠሉ በፊቱ ይሸማቀቃሉ፤
የሚደርስባቸውም ነገር* ዘላለማዊ ነው።