መዝሙር
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የቆሬ ልጆች+ ማህሌት።
49 እናንተ ሕዝቦች ሁሉ፣ ይህን ስሙ።
3 አፌ ጥበብን ይናገራል፤
በልቤም የማሰላስለው ነገር+ ማስተዋልን ይገልጣል።
4 ጆሮዬን ወደ ምሳሌ አዘነብላለሁ፤
እንቆቅልሼንም በበገና እፈታለሁ።
በታላቅ ብልጽግናቸው የሚኩራሩትንም+ ለምን እፈራለሁ?
7 አንዳቸውም ቢሆኑ ሌላውን ሰው መዋጀት፣
ወይም ለእሱ ቤዛ የሚሆን ነገር ለአምላክ መክፈል ጨርሶ አይችሉም፤+
8 (ለሕይወታቸው* የሚከፈለው የቤዛ* ዋጋ እጅግ ውድ ስለሆነ
መቼም ቢሆን ከአቅማቸው በላይ ነው)፤
11 ምኞታቸው ቤቶቻቸው ለዘላለም እንዲኖሩ፣
ድንኳናቸውም ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ነው።
ርስታቸውን በራሳቸው ስም ሰይመዋል።
13 የሞኞች መንገድ ይህ ነው፤+
እነሱ በሚናገሩት ከንቱ ቃል ተደስተው የሚከተሏቸው ሰዎች መንገድም ይኸው ነው። (ሴላ)
14 ለእርድ እንደሚነዱ በጎች ወደ መቃብር* እንዲወርዱ ተፈርዶባቸዋል።
ሞት እረኛቸው ይሆናል፤
በማለዳ ቅኖች ይገዟቸዋል።+
18 በሕይወት ዘመኑ ራሱን* ሲያወድስ ይኖራልና።+
(ስትበለጽግ ሰዎች ያወድሱሃል።)+
19 መጨረሻ ላይ ግን ከአባቶቹ ትውልድ ጋር ይቀላቀላል።
ከዚያ በኋላ ፈጽሞ ብርሃን አያዩም።
20 የተከበረ ቢሆንም እንኳ ይህን የማይረዳ ሰው
ከሚጠፉ እንስሳት ምንም አይሻልም።+