ኤርምያስ
1 በቢንያም አገር በአናቶት+ ከነበሩት ካህናት አንዱ የሆነው የኬልቅያስ ልጅ የኤርምያስ* ቃል ይህ ነው። 2 የይሁዳ ንጉሥ የአምዖን+ ልጅ ኢዮስያስ+ በነገሠ በ13ኛው ዓመት የይሖዋ ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ። 3 ደግሞም በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮዓቄም+ ዘመን፣ እንዲሁም የይሁዳ ንጉሥ የኢዮስያስ ልጅ የሴዴቅያስ+ 11ኛው ዓመት የግዛት ዘመን እስካበቃበት ጊዜ ድረስ ይኸውም ኢየሩሳሌም ወደ ግዞት እስከተወሰደችበት እስከ አምስተኛው ወር+ ድረስ ቃሉ ወደ እሱ መጣ።
4 የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦
ለብሔራት ነቢይ አድርጌሃለሁ።”
6 እኔ ግን “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ወዮልኝ!
እኔ ገና ልጅ* ስለሆንኩ+ ምን ብዬ እንደምናገር አላውቅም”+ አልኩ።
7 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦
“‘እኔ ገና ልጅ ነኝ’ አትበል።
ወደምልክህ ሁሉ ትሄዳለህና፤
የማዝህንም ሁሉ ትናገራለህ።+
9 ከዚያም ይሖዋ እጁን ዘርግቶ አፌን ዳሰሰ።+ ይሖዋም እንዲህ አለኝ፦ “ቃሌን በአፍህ አኑሬአለሁ።+ 10 እንግዲህ እንድትነቅልና እንድታፈርስ፣ እንድታጠፋና እንድታወድም፣ እንድትገነባና እንድትተክል ዛሬ በብሔራትና በመንግሥታት ላይ ሾሜሃለሁ።”+
11 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ “ኤርምያስ፣ የምታየው ምንድን ነው?” እኔም “የአልሞንድ ዛፍ* ቅርንጫፍ አያለሁ” አልኩ።
12 ይሖዋም እንዲህ አለኝ፦ “በትክክል አይተሃል፤ እኔ ቃሌን ለመፈጸም በከፍተኛ ንቃት እየተጠባበቅኩ ነውና።”
13 የይሖዋ ቃል ለሁለተኛ ጊዜ ወደ እኔ መጥቶ “ምን ይታይሃል?” አለኝ። እኔም “የተጣደ* ድስት* አያለሁ፤ አፉም ከሰሜን ወደ ደቡብ ያዘነበለ ነው” አልኩ። 14 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦
“በምድሪቱ ነዋሪዎች ሁሉ ላይ
ከሰሜን ጥፋት ይመጣል።+
15 ‘በሰሜን ያሉትን መንግሥታት ነገዶች ሁሉ እጠራለሁና’ ይላል ይሖዋ፤+
‘እነሱም ይመጣሉ፤ እያንዳንዱም ዙፋኑን
በኢየሩሳሌም በሮች መግቢያ፣+
በቅጥሮቿ ዙሪያ ሁሉና
በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ላይ ያደርጋል።+
16 ደግሞም እኔን ስለተዉ፣+
ለሌሎች አማልክትም የሚጨስ መሥዋዕት ስለሚያቀርቡና+
በገዛ እጃቸው ለሠሯቸው ነገሮች ስለሚሰግዱ+
በክፋታቸው ሁሉ ላይ ፍርዴን አውጃለሁ።’
17 አንተ ግን ለሥራ ተዘጋጅ፤*
ደግሞም ተነስ፤ እኔ የማዝህንም ሁሉ ንገራቸው።
እኔ ራሴ በፊታቸው እንዳላሸብርህ፣
እነሱን አትፍራቸው።+