ኤርምያስ
31 “በዚያን ጊዜ” ይላል ይሖዋ፣ “ለእስራኤል ወገኖች ሁሉ አምላክ እሆናለሁ፤ እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።”+
2 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
“እስራኤል ወደ ማረፊያ ቦታው በሄደ ጊዜ፣
ከሰይፍ የተረፉት ሰዎች በምድረ በዳ የአምላክን ሞገስ አገኙ።”
3 ይሖዋ ከሩቅ ተገለጠልኝ፤ እንዲህም አለኝ፦
“በዘላለማዊ ፍቅር ወድጄሻለሁ።
ከዚህም የተነሳ በታማኝ ፍቅር ወደ እኔ ሳብኩሽ።*+
4 አሁንም መልሼ እገነባሻለሁ፤ አንቺም ዳግመኛ ትገነቢያለሽ።+
6 በኤፍሬም ተራሮች የሚገኙ ጠባቂዎች
‘ተነሱ፤ ወደ ጽዮን፣ ወደ አምላካችን ወደ ይሖዋ እንውጣ’ ብለው የሚጮኹበት ቀን ይመጣልና።”+
7 ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦
“በታላቅ ደስታ ወደ ያዕቆብ ጩኹ።
ከብሔራት በላይ ስለሆናችሁ እልል በሉ።+
ይህን አውጁ፤ ውዳሴ አቅርቡ፤
ደግሞም ‘ይሖዋ ሆይ፣ ሕዝብህን፣ የእስራኤልን ቀሪዎች አድን’ በሉ።+
8 ከሰሜን ምድር መልሼ አመጣቸዋለሁ።+
ከምድር ዳርቻዎች እሰበስባቸዋለሁ።+
በመካከላቸው ዓይነ ስውርና አንካሳ፣+
ነፍሰ ጡርና ልትወልድ የተቃረበች ሴት በአንድነት ይገኛሉ።
ታላቅ ጉባኤ ሆነው ወደዚህ ይመለሳሉ።+
9 እያለቀሱ ይመጣሉ።+
ሞገስ ለማግኘት ሲለምኑ እየመራሁ አመጣቸዋለሁ።
እኔ ለእስራኤል አባት ነኝና፤ ኤፍሬምም የበኩር ልጄ ነው።”+
10 እናንተ ብሔራት፣ የይሖዋን ቃል ስሙ፤
ርቀው በሚገኙ ደሴቶችም ቃሉን አውጁ፦+
“እስራኤልን የበተነው እሱ ይሰበስበዋል።
መንጋውን እንደሚጠብቅ እረኛ ይጠብቀዋል።+
12 እነሱም መጥተው በጽዮን ከፍ ያለ ቦታ በደስታ እልል ይላሉ፤+
ደግሞም በይሖዋ ጥሩነት፣*
በእህሉ፣ በአዲሱ የወይን ጠጅ፣+ በዘይቱ
እንዲሁም በመንጎቹ ግልገሎችና በከብቶቹ ጥጆች የተነሳ ፊታቸው ይፈካል።+
13 “በዚያን ጊዜ ድንግሊቱ በደስታ ትጨፍራለች፤
ወጣቶቹና ሽማግሌዎቹም በአንድነት በደስታ ይጨፍራሉ።+
ሐዘናቸውን ወደ ሐሴት እለውጠዋለሁ።+
ከሐዘናቸው ተላቀው እንዲጽናኑና ደስ እንዲሰኙ አደርጋለሁ።+
15 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
‘የዋይታና የመራራ ለቅሶ ድምፅ በራማ+ ተሰማ፦
ወንዶች ልጆቿ ስለሌሉ
ከደረሰባት ሐዘን ለመጽናናት እንቢ አለች።’”+
16 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
“‘አታልቅሺ፤ ዓይኖችሽም እንባ አያፍስሱ፤
ሥራሽ ወሮታ አለውና’ ይላል ይሖዋ።
‘ከጠላት ምድር ይመለሳሉ።’+
17 ‘አንቺም ብሩህ ተስፋ ይጠብቅሻል’+ ይላል ይሖዋ።
‘ወንዶች ልጆችሽ ወደ ገዛ ምድራቸው ይመለሳሉ።’”+
መልሰኝ፤ እኔም ወዲያውኑ እመለሳለሁ፤
አንተ አምላኬ ይሖዋ ነህና።
አፈርኩ፤ ተዋረድኩም፤+
በወጣትነቴ የደረሰብኝን ነቀፋ ተሸክሜአለሁና።’”
20 “ኤፍሬም ከፍ አድርጌ የምመለከተው ውድ ልጄ አይደለም?+
ብዙ ጊዜ እሱን ተቃውሜ የምናገረውን ያህል፣ አሁንም አስበዋለሁና።
አንጀቴ ለእሱ የሚንሰፈሰፈው ለዚህ ነው።+
ደግሞም እራራለታለሁ” ይላል ይሖዋ።+
21 “የጎዳና ምልክቶችን ለራስሽ አቁሚ፤
መንገድ የሚጠቁሙ ዓምዶችን ትከዪ።+
የምትሄጂበትን አውራ ጎዳና ልብ ብለሽ ተመልከቺ።+
የእስራኤል ድንግል ሆይ፣ ተመለሽ፤ የራስሽ ወደሆኑት ወደነዚህ ከተሞች ተመለሽ።
22 ከዳተኛዪቱ ሴት ልጅ ሆይ፣ የምትወላውዪው እስከ መቼ ድረስ ነው?
ይሖዋ በምድር ላይ አዲስ ነገር ፈጥሯልና፦
ሴት ወንድን አጥብቃ ታሳድዳለች።”
23 የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የተማረኩባቸውን ሰዎች በምሰበስብበት ጊዜ በይሁዳ ምድርና በከተሞቹ ‘አንተ ጻድቅ መኖሪያ፣+ አንተ ቅዱስ ተራራ፣+ ይሖዋ ይባርክህ’ የሚል ቃል እንደገና ይናገራሉ። 24 በእሷም ውስጥ ይሁዳና ከተሞቹ ሁሉ እንዲሁም ገበሬዎችና የመንጋ እረኞች በአንድነት ይኖራሉ።+ 25 የዛለውን* አድሳለሁና፤ የደከመውንም* ሁሉ አበረታለሁ።”+
26 በዚህ ጊዜ ነቃሁ፤ ዓይኔንም ገለጥኩ፤ እንቅልፌም ጣፋጭ ሆኖልኝ ነበር።
27 “እነሆ፣ በእስራኤል ቤትና በይሁዳ ቤት የሰውን ዘርና የከብትን ዘር የምዘራበት ጊዜ ይመጣል” ይላል ይሖዋ።+
28 “እነሱን ለመንቀል፣ ለማፍረስ፣ ለማውደም፣ ለማጥፋትና ለመደምሰስ እከታተላቸው እንደነበረ ሁሉ፣+ እነሱን ለመገንባትና ለመትከልም እከታተላቸዋለሁ”+ ይላል ይሖዋ። 29 “በዚያም ዘመን ‘የሚጎመዝዝ ወይን የበሉት አባቶች ሆነው ሳለ የልጆቹ ጥርስ ጠረሰ’*+ ብለው ዳግመኛ አይናገሩም። 30 ከዚህ ይልቅ በዚያ ጊዜ እያንዳንዱ ሰው በገዛ በደሉ ይሞታል። የሚጎመዝዝ ወይን የሚበላ ሰው ሁሉ፣ የገዛ ራሱ ጥርስ ይጠርሳል።”
31 “እነሆ፣ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት ጊዜ ይመጣል” ይላል ይሖዋ።+ 32 “ይህም ቃል ኪዳን አባቶቻቸውን እጃቸውን ይዤ ከግብፅ ምድር እየመራሁ ባወጣኋቸው ቀን ከእነሱ ጋር እንደገባሁት ዓይነት ቃል ኪዳን አይሆንም፤+ ‘እኔ እውነተኛ ጌታቸው* ብሆንም እንኳ እነሱ ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋል’ ይላል ይሖዋ።”+
33 “ከዚያ ጊዜ በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና” ይላል ይሖዋ። “ሕጌን በውስጣቸው አኖራለሁ፤+ በልባቸውም እጽፈዋለሁ።+ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።”+
34 “እነሱም እያንዳንዳቸው ባልንጀራቸውን፣ እያንዳንዳቸውም ወንድማቸውን ‘ይሖዋን እወቅ!’ ብለው ከእንግዲህ አያስተምሩም፤+ ከትንሹ አንስቶ እስከ ትልቁ ድረስ ሁሉም ያውቁኛልና”+ ይላል ይሖዋ። “በደላቸውን ይቅር እላለሁና፤ ኃጢአታቸውንም ከእንግዲህ አላስታውስም።”+
35 ስሙ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ የሆነው፣
በቀን እንድታበራ ፀሐይን የሰጠው፣
በሌሊትም እንዲያበሩ የጨረቃንና የከዋክብትን ሕጎች ያወጣው፣*
ባሕሩን የሚያናውጠውና ኃይለኛ ማዕበል የሚያስነሳው
ይሖዋ እንዲህ ይላል፦+
36 “‘የእስራኤል ዘር ምንጊዜም በፊቴ የሚኖር ብሔር መሆኑ የሚያከትመው’ ይላል ይሖዋ፣
‘ይህ ሥርዓት ከተሻረ ብቻ ነው።’”+
37 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “‘መላውን የእስራኤል ዘር፣ በሠሩት ነገር ሁሉ የተነሳ ልተዋቸው የምችለው፣ በላይ ያሉትን ሰማያት መለካት፣ በታች ያሉትንም የምድር መሠረቶች መመርመር የሚቻል ከሆነ ብቻ ነው’ ይላል ይሖዋ።”+
38 “እነሆ፣ ከተማዋ ከሃናንኤል ማማ+ እስከ ማዕዘን በር+ ድረስ ለይሖዋ የምትገነባበት ጊዜ ይመጣል”+ ይላል ይሖዋ። 39 “የመለኪያ ገመዱም+ በቀጥታ ወደ ጋሬብ ኮረብታ ይዘረጋል፤ ደግሞም ወደ ጎዓ ይዞራል። 40 ሬሳና አመድ* ያለበት ሸለቆ* ሁሉ እንዲሁም የቄድሮንን ሸለቆ+ ይዞ በምሥራቅ በኩል እስካለው እስከ ፈረስ በር+ ማዕዘን ድረስ ያለው ደልዳላ ቦታ ሁሉ ለይሖዋ የተቀደሰ ይሆናል።+ ከእንግዲህ ወዲህ አይነቀልም ወይም አይወድምም።”