ሚልክያስ
4 “እነሆ፣ ያ ቀን እንደ ምድጃ እየነደደ ይመጣል፤+ በዚያ ጊዜ እብሪተኞች ሁሉና ክፉ አድራጊዎች በሙሉ እንደ ገለባ ይሆናሉ። የሚመጣው ቀን በእርግጥ ይበላቸዋል” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤ “ሥርም ሆነ ቅርንጫፍ አይተውላቸውም። 2 ስሜን ለምታከብሩት* ለእናንተ ግን የጽድቅ ፀሐይ በጨረሮቿ* ፈውስ ይዛ ትወጣለች፤ እናንተም እንደሰቡ ጥጆች ትቦርቃላችሁ።”
3 “እኔም እርምጃ በምወስድበት ቀን ክፉዎችን ትረግጣላችሁ፤ ከእግራችሁ ሥር እንዳለ አቧራ ይሆናሉና” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።
4 “የአገልጋዬን የሙሴን ሕግ ይኸውም መላው እስራኤል እንዲያከብረው በኮሬብ ያዘዝኩትን ሥርዓትና ድንጋጌ አስታውሱ።+
5 “እነሆ፣ ታላቁና የሚያስፈራው የይሖዋ ቀን ከመምጣቱ በፊት+ ነቢዩ ኤልያስን እልክላችኋለሁ።+ 6 እሱም መጥቼ ምድርን እንዳልመታና ፈጽሜ እንዳላጠፋ የአባቶችን ልብ እንደ ልጆች ልብ፣+ የልጆችንም ልብ እንደ አባቶች ልብ ያደርጋል።”*
(የዕብራይስጥና የአረማይክ ቅዱሳን መጻሕፍት ትርጉም እዚህ ላይ ተደመደመ፤ ከዚህ በኋላ ያሉት የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ናቸው)