ኤርምያስ
7 ከይሖዋ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፦ 2 “በይሖዋ ቤት በር ላይ ቆመህ በዚያ ይህን መልእክት አውጅ፦ ‘ለይሖዋ ለመስገድ በእነዚህ በሮች የምትገቡ የይሁዳ ሰዎች ሁሉ፣ የይሖዋን ቃል ስሙ። 3 የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “መንገዳችሁንና ተግባራችሁን አስተካክሉ፤ እኔም በዚህ ስፍራ እንድትኖሩ እፈቅድላችኋለሁ።+ 4 ‘ይህ* የይሖዋ ቤተ መቅደስ፣ የይሖዋ ቤተ መቅደስ፣ የይሖዋ ቤተ መቅደስ ነው!’ እያላችሁ በአሳሳች ቃል አትታመኑ።+ 5 በእርግጥ መንገዳችሁንና ተግባራችሁን ብታስተካክሉ፣ በሰውና በባልንጀራው መካከል ፍትሕ ብታሰፍኑ፣+ 6 ከባዕድ አገር የመጣውን ሰው፣ ወላጅ አልባ የሆኑ ልጆችንና* መበለቶችን ባትጨቁኑ፣+ በዚህ ቦታ የንጹሕ ሰው ደም ባታፈሱ እንዲሁም ጉዳት ላይ የሚጥሏችሁን ሌሎች አማልክት ባትከተሉ፣+ 7 በዚህች ስፍራ፣ ለአባቶቻችሁ በሰጠኋቸው በዚህ ምድር ለዘለቄታው እንድትኖሩ እፈቅድላችኋለሁ።”’”
8 “እናንተ ግን አሳሳች በሆነ ቃል ታምናችኋል፤+ ይህ ደግሞ ፈጽሞ አይጠቅማችሁም። 9 እየሰረቃችሁ፣+ እየገደላችሁ፣ እያመነዘራችሁ፣ በሐሰት እየማላችሁ፣+ ለባአል መሥዋዕት* እያቀረባችሁና+ የማታውቋቸውን አማልክት እየተከተላችሁ፣ 10 በስሜ ወደሚጠራው ወደዚህ ቤት መጥታችሁ በፊቴ መቆምና እነዚህን ሁሉ አስጸያፊ ነገሮች እያደረጋችሁ ‘ምንም ችግር አይደርስብንም’ ማለት ትችላላችሁ? 11 ስሜ የሚጠራበት ይህ ቤት በእናንተ ዓይን የዘራፊዎች ዋሻ ሆኗል ማለት ነው?+ እነሆ፣ እኔ ራሴ ይህን አይቻለሁ” ይላል ይሖዋ።
12 “‘አሁን ግን መጀመሪያ የስሜ ማደሪያ+ አድርጌው ወደነበረው በሴሎ+ ወዳለው ስፍራዬ ሂዱ፤ ከሕዝቤ ከእስራኤል ክፋት የተነሳም ምን እንዳደረግኩት እዩ።+ 13 እናንተ ግን እነዚህን ሁሉ ነገሮች መሥራታችሁን ቀጠላችሁ’ ይላል ይሖዋ፤ ‘ለእናንተ ደግሜ ደጋግሜ* ብናገርም እንኳ አልሰማችሁም።+ ደጋግሜ ጠራኋችሁ፤ እናንተ ግን መልስ አትሰጡም።+ 14 ስለዚህ በሴሎ እንዳደረግኩት ሁሉ በስሜ በተጠራው፣+ እናንተም በምትታመኑበት በዚህ ቤት+ ላይ እንዲሁም ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በሰጠሁት በዚህ ቦታ ላይ እንዲሁ አደርጋለሁ።+ 15 ወንድሞቻችሁን ሁሉ ይኸውም መላውን የኤፍሬም ዘር እንዳስወገድኩ እናንተንም ከፊቴ አስወግዳችኋለሁ።’+
16 “አንተም ለዚህ ሕዝብ አትጸልይ። እኔ ስለማልሰማህ+ ስለ እነሱ የልመና ጩኸትም ሆነ ጸሎት አታሰማ ወይም እኔን አትማጸን።+ 17 በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ የሚያደርጉትን አታይም? 18 እኔን ያሳዝኑ ዘንድ ‘ለሰማይ ንግሥት’* መሥዋዕት የሚሆን ቂጣ ለመጋገር ወንዶች ልጆች እንጨት ይሰበስባሉ፣ አባቶች እሳት ያቀጣጥላሉ፣ ሚስቶች ደግሞ ሊጥ ያቦካሉ፤+ ለሌሎች አማልክትም የመጠጥ መባ ያፈሳሉ።+ 19 ‘ለመሆኑ የሚጎዱት* እኔን ነው?’ ይላል ይሖዋ። ‘በራሳቸው ላይ ውርደት በማምጣት የሚጎዱት ራሳቸውን አይደለም?’+ 20 ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ንዴቴና ቁጣዬ በዚህ ቦታ፣ በሰውና በእንስሳ፣ በዱር ዛፎችና በምድሪቱ ፍሬ ላይ ይፈስሳል፤+ ቁጣዬ ይነድዳል፤ ፈጽሞም አይጠፋም።’+
21 “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የጀመራችሁትን ግፉበት፤ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎቻችሁን በሌሎች መሥዋዕቶቻችሁ ላይ ጨምሩ፤ ሥጋውንም ራሳችሁ ብሉ።+ 22 አባቶቻችሁን ከግብፅ ምድር ባወጣኋቸው ጊዜ ሙሉ በሙሉ ስለሚቃጠሉ መባዎችና መሥዋዕቶች አልነገርኳቸውም ወይም አላዘዝኳቸውም።+ 23 ከዚህ ይልቅ ይህን ትእዛዝ ሰጥቻቸው ነበር፦ “ድምፄን ስሙ፤ እኔም አምላካችሁ እሆናለሁ፤ እናንተም ሕዝቤ ትሆናላችሁ።+ መልካም እንዲሆንላችሁ በማዛችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ።”’+ 24 እነሱ ግን አልሰሙም ወይም ጆሯቸውን አልሰጡም፤+ ይልቁንም ግትር ሆነው ክፉ ልባቸውን በመከተል በገዛ ራሳቸው ዕቅድ* ሄዱ፤+ ወደ ፊት በመሄድ ፋንታ ወደ ኋላ ተመለሱ፤ 25 አባቶቻችሁ ከግብፅ ምድር ከወጡበት ጊዜ አንስቶ እስከዚህ ቀን ድረስ ይህን አደረጉ።+ በመሆኑም አገልጋዮቼ የሆኑትን ነቢያት ሁሉ ወደ እናንተ መላኬን ቀጠልኩ፤ ደግሜ ደጋግሜ በየዕለቱ* ላክኋቸው።+ 26 እነሱ ግን እኔን ለመስማት እንቢተኛ ሆኑ፤ ጆሯቸውንም አልሰጡም።+ ይልቁንም ግትር ሆኑ፤* አባቶቻቸው ከሠሩት የከፋ ነገር አደረጉ!
27 “ይህን ሁሉ ቃል ትነግራቸዋለህ፤+ እነሱ ግን አይሰሙህም፤ ትጠራቸዋለህ፤ እነሱ ግን አይመልሱልህም። 28 እንዲህም ትላቸዋለህ፦ ‘ይህ ብሔር የአምላኩን የይሖዋን ድምፅ አልሰማም፤ ተግሣጽ ለመቀበልም እንቢተኛ ሆኗል። ታማኝነት ጠፍቷል፤ በመካከላቸውም ጨርሶ አይነሳም።’*+
29 “ያልተቆረጠውን* ፀጉርሽን ሸልተሽ ጣይው፤ በተራቆቱት ኮረብቶችም ላይ ሙሾ አውርጂ፤* ይሖዋ እጅግ ያስቆጣውን ይህን ትውልድ ጥሎታልና፤ እርግፍ አድርጎም ይተወዋል። 30 ‘የይሁዳ ሰዎች በፊቴ መጥፎ ነገር ሠርተዋልና’ ይላል ይሖዋ። ‘አስጸያፊ ጣዖቶቻቸውን በስሜ በተጠራው ቤት ውስጥ በማስቀመጥ አርክሰውታል።+ 31 ያላዘዝኩትንና በልቤ እንኳ ፈጽሞ ያላሰብኩትን* ነገር ለማድረግ ይኸውም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በእሳት ለማቃጠል+ በሂኖም ልጅ ሸለቆ*+ የሚገኘውን የቶፌትን ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎች ሠርተዋል።’+
32 “‘ከዚህ የተነሳ፣’ ይላል ይሖዋ፣ ‘የእርድ ሸለቆ እንጂ ቶፌት ወይም የሂኖም ልጅ ሸለቆ* ተብሎ የማይጠራበት ጊዜ ይመጣል። እነሱም ቦታ እስኪታጣ ድረስ በቶፌት ይቀብራሉ።+ 33 የዚህ ሕዝብ አስከሬንም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ሲሳይ ይሆናል፤ ፈርተው እንዲሸሹ የሚያደርጋቸውም የለም።+ 34 የሐሴትንና የደስታን ድምፅ እንዲሁም የሙሽራንና የሙሽሪትን ድምፅ፣ ከይሁዳ ከተሞችና ከኢየሩሳሌም ጎዳናዎች አጠፋለሁ፤+ ምድሪቱ የፍርስራሽ ክምር ትሆናለችና።’”+