ኤርምያስ
6 እናንተ የቢንያም ልጆች፣ ተሸሸጉ፤ ከኢየሩሳሌም ወጥታችሁ ሽሹ።
ከሰሜን ጥፋት፣ ይኸውም ታላቅ መዓት እያንዣበበ ነውና።+
2 የጽዮን ሴት ልጅ ያማረችና ቅምጥል ሴት ትመስላለች።+
3 እረኞችና መንጎቻቸው ይመጣሉ።
4 “በእሷ ላይ ጦርነት ለማወጅ ተዘጋጁ!*
ተነሱ፣ እኩለ ቀን ላይ ጥቃት እንሰንዝርባት!”
“ወዮልን፣ ቀኑ እየመሸ፣
የምሽቱም ጥላ እየረዘመ ነውና!”
5 “ተነሱ፣ በሌሊት ጥቃት እንሰንዝርባት፤
የማይደፈሩትንም ማማዎቿን እንደምስስ።”+
6 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦
“እንጨት ቁረጡ፤ በኢየሩሳሌም ዙሪያም የአፈር ቁልል ደልድሉ።+
ይህች ከተማ ተጠያቂ ልትሆን ይገባል፤
በውስጧ ከግፍ በቀር ምንም አይገኝም።+
7 የውኃ ጉድጓድ ውኃውን እንደቀዘቀዘ እንደሚያቆይ፣
እሷም ክፋቷን እንዳለ ጠብቃ አቆይታለች።
ዓመፅና ጥፋት በውስጧ ይሰማል፤+
ሕመምና ደዌ ምንጊዜም በፊቴ ናቸው።
9 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
“የእስራኤልን ቀሪዎች በወይን ተክል ላይ እንደቀሩ የመጨረሻ የወይን ፍሬዎች ምንም ሳያስቀሩ ይቃርሟቸዋል።
ከወይን ተክሎች ላይ የወይን ፍሬዎች እንደሚለቅም ሰው በድጋሚ እጅህን ዘርጋ።”
10 “ለማን ልናገር? ማንን ላስጠንቅቅ?
ማንስ ይሰማል?
እነሆ፣ ጆሮዎቻቸው ስለተዘጉ* ማዳመጥ አይችሉም።+
እነሆ፣ የይሖዋን ቃል መሳለቂያ አድርገውታል፤+
ቃሉም ደስ አያሰኛቸውም።
11 በመሆኑም በይሖዋ ቁጣ ተሞልቻለሁ፤
በውስጤ አፍኜ ስለያዝኩት ዝያለሁ።”+
“በጎዳና ባለ ልጅ፣
ተሰብስበው ባሉ ወጣቶች ላይ አፍስሰው።+
12 ቤቶቻቸው፣ እርሻዎቻቸውና ሚስቶቻቸው
ለሌሎች ይሰጣሉ።+
እጄን በምድሪቱ ነዋሪዎች ላይ እዘረጋለሁና” ይላል ይሖዋ።
14 ሰላም ሳይኖር፣
‘ሰላም ነው! ሰላም ነው!’ እያሉ
የሕዝቤን ስብራት* ላይ ላዩን* ለመጠገን ይሞክራሉ።+
15 በፈጸሙት አስጸያፊ ተግባር ኀፍረት ተሰምቷቸዋል?
እነሱ እንደሆነ ጨርሶ ኀፍረት አይሰማቸውም!
ውርደት ምን ማለት እንደሆነ እንኳ አያውቁም!+
ስለዚህ ከወደቁት ጋር ይወድቃሉ።
እነሱን በምቀጣበት ጊዜ ይሰናከላሉ” ይላል ይሖዋ።
16 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
“መስቀለኛ መንገዶቹ ላይ ቁሙና ተመልከቱ።
እነሱ ግን “በዚያ አንሄድም” ይላሉ።+
እነሱ ግን “አናዳምጥም” አሉ።+
18 “ስለዚህ እናንተ ብሔራት፣ ስሙ!
እናንተ ሰዎች ሆይ፣
ምን እንደሚደርስባቸው እወቁ።
19 ምድር ሆይ፣ ስሚ!
ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባችሁን አልቀበልም፤
መሥዋዕቶቻችሁም ደስ አያሰኙኝም።”+
21 ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
22 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
“እነሆ፣ ከሰሜን ምድር አንድ ሕዝብ እየመጣ ነው፤
ከምድር ዳርቻም ታላቅ ብሔር ይነሳል።+
23 ቀስትና ጦር ይይዛሉ።
ጨካኝና ምሕረት የለሽ ናቸው።
ድምፃቸው እንደ ባሕር ያስተጋባል፤
ፈረሶችንም ይጋልባሉ።+
የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ ልክ እንደ ተዋጊ በአንቺ ላይ ይሰለፋሉ።”
24 ወሬውን ሰምተናል።
25 ወደ ውጭ አትውጡ፤
በመንገዱም ላይ አትዘዋወሩ፤
ጠላት ሰይፍ ታጥቋልና፤
በየቦታውም ሽብር ነግሦአል።
26 የሕዝቤ ሴት ልጅ ሆይ፣
ማቅ ልበሺ፤+ በአመድም ላይ ተንከባለዪ።
እንደ መዳብና ብረት ናቸው፤
ሁሉም ምግባረ ብልሹዎች ናቸው።
29 ወናፎቹ በእሳት ተቃጠሉ።
ከእሳቱም የሚወጣው እርሳስ ነው።
30 ሰዎች ‘የተጣለ ብር’ ብለው ይጠሯቸዋል፤
ይሖዋ ጥሏቸዋልና።”+