ዕንባቆም
1 ነቢዩ ዕንባቆም* በራእይ የተቀበለው መልእክት፦
2 ይሖዋ ሆይ፣ እርዳታ ለማግኘት ስጮኽ የማትሰማው እስከ መቼ ነው?+
ከግፍ እንድታስጥለኝ ስለምን ጣልቃ የማትገባው እስከ መቼ ነው?*+
3 ለምን በደል ሲፈጸም እንዳይ ታደርገኛለህ?
ጭቆናንስ ለምን ዝም ብለህ ታያለህ?
ጥፋትና ግፍ በፊቴ የሚፈጸመው ለምንድን ነው?
ጠብና ግጭትስ ለምን በዛ?
4 ስለዚህ ሕግ ላልቷል፤
ፍትሕም ጨርሶ የለም።
ክፉው ጻድቁን ከቦታልና፤
ከዚህ የተነሳ ፍትሕ ተጣሟል።+
5 “ብሔራትን እዩ፣ ደግሞም ልብ በሉ!
የእነሱ ያልሆኑ ቤቶችን ለመውረስ፣
ሰፋፊ የምድር ክፍሎችን ይወራሉ።+
7 እነሱ አስደንጋጭና አስፈሪ ናቸው።
የጦር ፈረሶቻቸው በፍጥነት ይጋልባሉ፤
ፈረሶቻቸው ከሩቅ ስፍራ ይመጣሉ።
ለመብላት እንደሚጣደፍ ንስር ተምዘግዝገው ይወርዳሉ።+
እንደ ምሥራቅ ነፋስ ፊታቸውን ያቀናሉ፤+
ምርኮኞችንም እንደ አሸዋ ያፍሳሉ።
በተመሸገ ስፍራ ሁሉ ላይ ይስቃሉ፤+
የአፈር ቁልልም ሠርተው ይይዙታል።
12 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ከዘላለም አንስቶ ያለህ አይደለህም?+
ቅዱስ የሆንከው አምላኬ ሆይ፣ አንተ አትሞትም።*+
14 ሰው እንደ ባሕር ዓሣ፣
ገዢም እንደሌላቸው መሬት ለመሬት የሚሳቡ ፍጥረታት እንዲሆን ለምን ትፈቅዳለህ?
15 እሱ* እነዚህን ሁሉ በመንጠቆ ጎትቶ ያወጣል።
በመረቡ ይይዛቸዋል፤
በዓሣ ማጥመጃ መረቡም ይሰበስባቸዋል።
በዚህም እጅግ ሐሴት ያደርጋል።+
17 ታዲያ መረቡን ሁልጊዜ ያራግፋል?*
ብሔራትንስ ያለርኅራኄ መፍጀቱን ይቀጥላል?+