ኤርምያስ
50 ይሖዋ በነቢዩ ኤርምያስ በኩል ስለ ባቢሎን+ ይኸውም ስለ ከለዳውያን ምድር የተናገረው ቃል ይህ ነው፦
2 “በብሔራት መካከል ይህን ተናገሩ፤ ደግሞም አውጁ።
ምልክት* አቁሙ፤ ይህን አውጁ።
ምንም ነገር አትደብቁ!
እንዲህም በሉ፦ ‘ባቢሎን ተይዛለች።+
ቤል ኀፍረት ተከናንቧል።+
ሜሮዳክ በፍርሃት ርዷል።
ምስሎቿ ተዋርደዋል።
አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቿ* ተሸብረዋል።’
3 ከሰሜን አንድ ብሔር በእሷ ላይ ተነስቷልና።+
እሱም ምድሪቷን አስፈሪ ቦታ ያደርጋታል፤
በእሷ ውስጥ የሚኖር ሰው የለም።
ሰውም ሆነ እንስሳ ሸሽቷል፤
አካባቢውን ለቀው ሄደዋል።”
4 “በእነዚያ ቀናትና በዚያ ጊዜ” ይላል ይሖዋ፣ “የእስራኤል ሕዝብም ሆነ የይሁዳ ሕዝብ በአንድነት ይመጣሉ።+ እያለቀሱ ይሄዳሉ፤+ በአንድነትም አምላካቸውን ይሖዋን ይፈልጋሉ።+ 5 ወደ ጽዮን የሚወስደውን መንገድ ይጠይቃሉ፤+ ፊታቸውንም ወደዚያ አቅጣጫ አዙረው ‘ኑ፣ ከይሖዋ ጋር የማይረሳ ዘላለማዊ ቃል ኪዳን እንግባ’ ይላሉ።+ 6 ሕዝቤ የጠፉ በጎች መንጋ ሆኗል።+ የገዛ እረኞቻቸው እንዲባዝኑ አድርገዋቸዋል።+ ወደ ተራሮች ነዷቸው፤ እነሱም በየተራራውና በየኮረብታው ተቅበዘበዙ። ማረፊያ ቦታቸውን ረሱ። 7 ያገኟቸውም ሁሉ ዋጧቸው፤+ ጠላቶቻቸውም ‘በይሖዋ ይኸውም የጽድቅ መኖሪያና የአባቶቻቸው ተስፋ በሆነው በይሖዋ ላይ ኃጢአት ስለሠሩ እኛ በደለኞች አይደለንም’ ብለዋል።”
9 እነሆ፣ እኔ ከሰሜን ምድር የታላላቅ ብሔራትን ጉባኤ አስነስቼ
በባቢሎን ላይ አመጣባታለሁና።+
እነሱም እሷን ለመውጋት ይሰለፋሉ፤
በዚያም በኩል ትያዛለች።
10 የከለዳውያን ምድር ትበዘበዛለች።+
የሚበዘብዟትም ሁሉ እስኪበቃቸው ድረስ ይመዘብሯታል”+ ይላል ይሖዋ።
በለምለም ሣር ላይ እንዳለች ጊደር ፈንጭታችኋልና፤
እንደ ድንጉላ ፈረሶችም አሽካክታችኋል።
12 እናታችሁ ለኀፍረት ተዳርጋለች።+
የወለደቻችሁም እጅግ አዝናለች።
እነሆ፣ ከብሔራት ሁሉ ያነሰች፣
ውኃ የሌለባት ምድረ በዳና በረሃ ሆናለች።+
በባቢሎን በኩል የሚያልፍ ሁሉ በፍርሃት አፍጥጦ ይመለከታታል፤
ከደረሱባትም መቅሰፍቶች ሁሉ የተነሳ ያፏጫል።+
14 እናንተ ደጋን የምትወጥሩ* ሁሉ፣
ባቢሎንን ለመውጋት በዙሪያዋ ተሰለፉ።
15 በዙሪያዋ ሁሉ ቀረርቶ አሰሙ።
እጇን ሰጥታለች።
እሷን ተበቀሏት።
እንዳደረገችው አድርጉባት።+
16 ዘር የሚዘራውንና
በመከር ወቅት ማጭድ የሚይዘውን ከባቢሎን አስወግዱ።+
ከጨካኙ ሰይፍ የተነሳ እያንዳንዱ ወደ ገዛ ሕዝቡ ይመለሳል፤
እያንዳንዱም ወደ ገዛ ምድሩ ይሸሻል።+
17 “የእስራኤል ሕዝብ የባዘነ በግ ነው።+ እንዲባዝን ያደረጉት አንበሶች ናቸው።+ በመጀመሪያ የአሦር ንጉሥ በላው፤+ ከዚያም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* አጥንቱን ቆረጣጠመው።+ 18 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ በአሦር ንጉሥ ላይ እንዳደረግኩት ሁሉ በባቢሎን ንጉሥና በምድሩ ላይ እንዲሁ አደርጋለሁ።+ 19 እስራኤልንም ወደ መሰማሪያው እመልሰዋለሁ፤+ እሱም በቀርሜሎስና በባሳን ይሰማራል፤+ በኤፍሬምና+ በጊልያድ+ ተራሮችም ላይ እስኪጠግብ ድረስ ይመገባል።’”*
20 “በእነዚያ ቀናትና በዚያ ጊዜ” ይላል ይሖዋ፣
“የእስራኤል በደል ይፈለጋል፤
ሆኖም አይገኝም፤
የይሁዳም ኃጢአት አይገኝም፤
እንዲተርፉ ያደረግኳቸውን ይቅር እላቸዋለሁና።”+
21 “በመረታይም ምድር ላይ ውጣ፤ በጰቆድ+ ነዋሪዎችም ላይ ተነሳ።
ነዋሪዎቹ ይጨፍጨፉ፤ ሙሉ በሙሉም ይጥፉ”* ይላል ይሖዋ።
“ያዘዝኩህንም ሁሉ አድርግ።
22 በምድሪቱ ላይ የጦርነትና
የታላቅ ጥፋት ድምፅ ይሰማል።
23 የምድር ሁሉ መዶሻ እንዴት ተቆረጠ! እንዴትስ ተሰበረ!+
ባቢሎን በብሔራት መካከል እንዴት መቀጣጫ ሆነች!+
24 ባቢሎን ሆይ፣ በአንቺ ላይ ወጥመድ ዘርግቻለሁ፤ ደግሞም ተይዘሻል፤
አንቺ ግን አልታወቀሽም።
ተገኘሽ፤ እንዲሁም ተያዝሽ፤+
የተቃወምሽው ይሖዋን ነውና።
25 ይሖዋ ግምጃ ቤቱን ከፍቷል፤
የቁጣ የጦር መሣሪያዎቹንም ያወጣል።+
ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ
በከለዳውያን ምድር የሚሠራው ሥራ አለና።
26 ከሩቅ ቦታ መጥታችሁ በእሷ ላይ ውጡ።+
ጎተራዎቿን ክፈቱ።+
እንደ እህል ክምር ከምሯት።
ፈጽማችሁ አጥፏት።+
አንድም ሰው አታስቀሩላት።
27 ወይፈኖቿን ሁሉ እረዱ፤+
ወደ እርድ ቦታ ይውረዱ።
ቀናቸው ይኸውም የሚመረመሩበት ጊዜ
ስለደረሰ ወዮላቸው!
28 የአምላካችንን የይሖዋን በቀል፣
ስለ ቤተ መቅደሱ ሲል የወሰደውን የበቀል እርምጃ+ በጽዮን ለማወጅ
ከባቢሎን ምድር የሚሸሹና
አምልጠው የሚሄዱ ሰዎች ድምፅ ይሰማል።
በዙሪያዋም ስፈሩ፤ አንድም ሰው እንዳያመልጥ።
እንደ ሥራዋ መልሱላት።+
እሷ እንዳደረገችው ሁሉ እናንተም እንዲሁ አድርጉባት።+
በይሖዋ ላይ ይኸውም በእስራኤል ቅዱስ ላይ
የእብሪት ድርጊት ፈጽማለችና።+
31 “አንቺ ዓመፀኛ፣+ እነሆ፣ እኔ በአንቺ ላይ ተነስቻለሁ”+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤
“ቀንሽ ይኸውም አንቺን ተጠያቂ የማደርግበት ጊዜ ይመጣልና።
32 አንቺ ዓመፀኛ ተሰናክለሽ ትወድቂያለሽ፤
የሚያነሳሽም አይኖርም።+
ከተሞችሽንም በእሳት አነዳለሁ፤
በዙሪያሽም ያለውን ሁሉ ይበላል።”
33 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
“የእስራኤል ሕዝብና የይሁዳ ሕዝብ ተጨቁነዋል፤
ማርከው የወሰዷቸውም ሁሉ ጠፍረው ይዘዋቸዋል።+
እነሱን ለመልቀቅ ፈቃደኞች አልሆኑም።+
34 ይሁንና የሚቤዣቸው ብርቱ ነው።+
ስሙ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ነው።+
35 “በከለዳውያን፣ በባቢሎን ነዋሪዎች፣ በመኳንንቷ
እንዲሁም በጥበበኞቿ ላይ ሰይፍ ተመዟል” ይላል ይሖዋ።+
36 “ከንቱ ነገር በሚናገሩ ሰዎች* ላይ ሰይፍ ተመዟል፤ እነሱም የሞኝነት ድርጊት ይፈጽማሉ።
በተዋጊዎቿ ላይ ሰይፍ ተመዟል፤ እነሱም በሽብር ይዋጣሉ።+
ውድ በሆኑ ሀብቶቿ ላይ ሰይፍ ተመዟል፤ እነሱም ይዘረፋሉ።+
የተቀረጹ ምስሎች ምድር ናትና፤+
አስፈሪ በሆኑት ራእዮቻቸው የተነሳ እንደ እብድ ያደርጋቸዋል።
39 ስለዚህ የበረሃ ፍጥረታት ከሚያላዝኑ እንስሳት ጋር ይኖራሉ፤
በእሷም ውስጥ ሰጎኖች ይኖራሉ።+
ከዚህ በኋላ የሚኖርባት አይገኝም፤
ከትውልድ እስከ ትውልድም ማንም አይቀመጥባትም።”+
40 “አምላክ ሰዶምንና ገሞራን+ እንዲሁም በአካባቢያቸው ያሉትን ከተሞች በደመሰሰ ጊዜ+ እንደሆነው ሁሉ” ይላል ይሖዋ፣ “በዚያ ማንም አይኖርም፤ አንድም ሰው በዚያ አይቀመጥም።+
ጨካኝና ምሕረት የለሽ ናቸው።+
ፈረሶቻቸውን እየጋለቡ ሲመጡ
ድምፃቸው እንደሚጮኽ ባሕር ነው።+
የባቢሎን ሴት ልጅ ሆይ፣ አንቺን ለመውጋት በአንድ ልብ ሆነው ይሰለፉብሻል።+
ጭንቀት ይይዘዋል፤
ልትወልድ እንደተቃረበች ሴት ይሠቃያል።
44 “እነሆ፣ አንድ ሰው፣ እንደ አንበሳ በዮርዳኖስ ዳርቻ ከሚገኙ ጥቅጥቅ ያሉ ጥሻዎች ወጥቶ አስተማማኝ በሆነው መሰማሪያ ላይ ይመጣል፤ እኔ ግን ወዲያውኑ ከእሷ አባርራቸዋለሁ። የተመረጠውን በእሷ ላይ እሾማለሁ።+ እንደ እኔ ያለ ማነው? ማንስ ሊሟገተኝ ይችላል? በእኔ ፊት ሊቆም የሚችል እረኛ የትኛው ነው?+ 45 ስለዚህ እናንተ ሰዎች፣ ይሖዋ በባቢሎን ላይ ያስተላለፈውን ውሳኔና*+ በከለዳውያን ምድር ላይ ያሰበውን ሐሳብ ስሙ።
ከመንጋው መካከል ትናንሽ የሆኑት ተጎትተው መወሰዳቸው አይቀርም።
ከእነሱ የተነሳ መሰማሪያቸውን ባድማ ያደርጋል።+
46 ባቢሎን ስትያዝ ከሚሰማው ድምፅ የተነሳ ምድር ትናወጣለች፤
ከብሔራትም መካከል ጩኸት ይሰማል።”+