ኤርምያስ
9 ምነው ራሴ በውኃ በተሞላ!
ዓይኖቼ የእንባ ምንጭ በሆኑ!+
ለታረዱት ወገኖቼ
ቀን ከሌት ባለቀስኩ ነበር።
2 ምነው በምድረ በዳ ለተጓዦች የሚሆን ማረፊያ ቦታ ባገኘሁ ኖሮ!
3 ምላሳቸውን እንደ ደጋን ወጠሩ፤
በምድሪቱ ላይ ታማኝነት ሳይሆን ውሸት ሰፍኗል።+
“በክፋት ላይ ክፋት እየጨመሩ ይሄዳሉ፤
እኔንም ጨርሶ አይሰሙም”+ ይላል ይሖዋ።
4 “እያንዳንዳችሁ ራሳችሁን ከባልንጀራችሁ ጠብቁ፤
ወንድማችሁን እንኳ ሳይቀር አትመኑ።
5 እያንዳንዱ ባልንጀራውን ያታልላል፤
አንድም ሰው እውነትን አይናገርም።
ምላሳቸውን ውሸት መናገር አስተምረውታል።+
ትክክል ያልሆነ ነገር በማድረግ ራሳቸውን ያደክማሉ።
6 የምትኖረው አታላይ በሆኑ ሰዎች መካከል ነው።
አታላይ ከመሆናቸውም የተነሳ እኔን ለማወቅ እንቢተኞች ሆነዋል” ይላል ይሖዋ።
7 ስለዚህ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
“እኔ አቀልጣቸዋለሁ፤ ደግሞም እፈትናቸዋለሁ፤+
ከሕዝቤ ሴት ልጅ ጋር በተያያዘ ከዚህ ሌላ ምን ማድረግ እችላለሁ?
8 ምላሳቸው ማታለያ የሚናገር፣ ገዳይ ፍላጻ ነው።
ሰው በአፉ ለባልንጀራው ስለ ሰላም ይናገራል፤
በውስጡ ግን ለማጥቃት ያደባል።”
9 “ታዲያ በእነዚህ ነገሮች የተነሳ ተጠያቂ ላደርጋቸው አይገባም?” ይላል ይሖዋ።
10 በተራሮቹ የተነሳ አለቅሳለሁ፤ ዋይ ዋይም እላለሁ፤
በምድረ በዳ ባሉት ማሰማሪያዎችም የተነሳ ሙሾ አወርዳለሁ፤*
ማንም ሰው እንዳያልፍባቸው በእሳት ተቃጥለዋልና፤
የከብቶችም ድምፅ አይሰማም።
የሰማይ ወፎችና የዱር አራዊት ሸሽተዋል፤ ከአካባቢው ጠፍተዋል።+
12 ይህን ይረዳ ዘንድ ጥበበኛ የሆነ ማን ነው?
ይህን ያሳውቅ ዘንድ የይሖዋ አፍ የተናገረው ለማን ነው?
ምድሪቱ የጠፋችው ለምንድን ነው?
ማንም እንዳያልፍባት
እንደ ምድረ በዳ የተለበለበችው ለምንድን ነው?”
13 ይሖዋ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “በፊታቸው ያኖርኩትን ሕጌን* ስለተዉና ስላልተከተሉ እንዲሁም ድምፄን ስላልሰሙ ነው። 14 ከዚህ ይልቅ ግትር ሆነው የገዛ ልባቸውን+ እንዲሁም አባቶቻቸው ባስተማሯቸው መሠረት የባአልን ምስሎች ተከተሉ።+ 15 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ይህ ሕዝብ ጭቁኝ እንዲበላ አደርጋለሁ፤ የተመረዘም ውኃ እንዲጠጣ አደርጋለሁ።+ 16 እነሱም ሆኑ አባቶቻቸው በማያውቋቸው ብሔራት መካከል እበትናቸዋለሁ፤+ ሙሉ በሙሉ እስካጠፋቸውም ድረስ ከኋላቸው ሰይፍን እሰዳለሁ።’+
17 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
‘በማስተዋል ተመላለሱ።
የሠለጠኑ አልቃሽ ሴቶችንም ልካችሁ አስመጡ፤
18 ዓይኖቻችን እንባ ያጎርፉ ዘንድ፣
ሽፋሽፍቶቻችንም ውኃ ያንጠባጥቡ ዘንድ
ፈጥነው እንዲመጡና የሐዘን እንጉርጉሮ እንዲያንጎራጉሩልን ጥሯቸው።+
19 ከጽዮን የሐዘን እንጉርጉሮ ድምፅ ተሰምቷልና፦+
“ከባድ ጥፋት ደርሶብናል!
ታላቅ ኀፍረት ተከናንበናል!
ምድሪቱን ጥለን ሄደናልና፤ እነሱም ቤቶቻችንን አፈራርሰዋል።”+
20 እናንተ ሴቶች፣ የይሖዋን ቃል ስሙ።
ጆሯችሁ የአፉን ቃል ያዳምጥ።
ሴቶች ልጆቻችሁን ይህን የሐዘን እንጉርጉሮ አስተምሯቸው፤
አንዳችሁም ለሌላው ይህን ሙሾ አስተምሩ።+
22 እንዲህ በል፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ሲል አውጇል፦
24 “ከዚህ ይልቅ የሚኩራራ በዚህ ነገር ይኩራራ፦
ስለ እኔ ጥልቅ ማስተዋልና እውቀት ያለው በመሆኑ+
እንዲሁም በምድር ላይ ታማኝ ፍቅር የማሳየው፣ ደግሞም ፍትሕና ጽድቅ የማሰፍነው እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ በማወቁ ይኩራራ፤+
በእነዚህ ነገሮች ደስ እሰኛለሁና”+ ይላል ይሖዋ።
25 “እነሆ፣ እንዲህ የሚሆንበት ቀን ይመጣል” ይላል ይሖዋ፣ “የተገረዘ ቢሆንም እንኳ ያልተገረዘውን ሁሉ ተጠያቂ አደርጋለሁ፤+ 26 ግብፅን፣+ ይሁዳን፣+ ኤዶምን፣+ አሞናውያንን፣+ ሞዓብንና+ በሰሪሳራቸው* ላይ ያለውን ፀጉር የሚላጩትን በምድረ በዳ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ተጠያቂ አደርጋለሁ፤+ ብሔራት ሁሉ ያልተገረዙ ናቸውና፤ የእስራኤልም ቤት ሁሉ ልባቸው ያልተገረዘ ነው።”+